
አቶ ጌታቸው አዲስ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸው ከተገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ መቀለ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲሞክራሲያዊ ማሻሻያዎችን ለማካሄድ እንደሚሰሩ ያመለከቱት አቶ ጌታቸው ረዳ በጦርነቱ ወቅት ለተከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመፈለግ እንደሚጥሩ እና በክልሉ ዘላቂ ሰላም ማምጣትም ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
Source: Link to the Post