You are currently viewing አነጋጋሪው መግለጫ በፅሁፍ እነ አቡነ ሳዊሮስ ወደቀደመ ክህነታቸው እና ሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መንገድ “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በፈጸሙት መካከል የ…

አነጋጋሪው መግለጫ በፅሁፍ እነ አቡነ ሳዊሮስ ወደቀደመ ክህነታቸው እና ሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መንገድ “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በፈጸሙት መካከል የ…

አነጋጋሪው መግለጫ በፅሁፍ እነ አቡነ ሳዊሮስ ወደቀደመ ክህነታቸው እና ሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መንገድ “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በፈጸሙት መካከል የተደረሰው ስምምነት ሙሉ መግለጫ:_ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን “ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት አለብኝ። እነርሱም ድምፄን ይሰማሉ። አንድ መንጋም ይሆናሉ። እረኛውም እንድ።” የዮሐንስ ወንጌል 10+16 ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያጋጠመውን ፈተና በመነጋገር ለመፍታት ከሁለቱም ወገን ያለን አባቶች ተገናኝተናል። በውይይታችንም የቤተ ክርስቲያንን እና የሀገርን አንድነት የሚያጸና፤ መለያየትን የሚያጠፋ፣ አገልግሎትን የሚያስፋ መንገድ መከተል መከተል እንደሚገባ አምነን፤ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ከቋንቋ እና ከአገልጋዮች ጋር በተያያዘ የሚነሡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከዚህ በፊት የተጀመሩ ጥረቶችን በማጠናከር፣ ጥያቄዎቹ በቤተ ክርስቲያን በኩል መመለስ እንዳለባቸው ተገንዝበን፤ የካቲት 8 ቀን 2015 ባደረግነው ውይይት የሚከተሉትን የመግባቢያ ሐሳቦች ላይ ደርሰናል። 1) በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፣ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር። ለዚህም ከዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ፣ 2) በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናት ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮችና በአገልግሎት እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከበፊቱ በበለጠ ተገቢው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ፣ 3) በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚያገለግሉ ቋንቋውን የሚያውቁ አገልጋዮችን የሚያሠለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ፣ የተከፈቱትም እንዲጠናከሩ እንዲደረግ። 4) ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በቂ የሆኑ የኦሮምኛ ቋንቋን የሚያውቁና በቋንቋው የሚያገለግሉ ኤጲስ ቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾሙ። 5) ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሀገረ ስብከታቸውና የክህነት ማዕረጋቸው እንዲመለሱ። 6) በሦስቱ አባቶች የተሾሙት አባቶች ቀድሞ ወደነበሩበት የክህነት ማዕረግ ይመለሳሉ። ከእነርሱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት እንደገና በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሾሙ ይደረጋል። 7) በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት የወንጌል አገልግሎትን በሚያጠናክር መልክ እናሻሽላለን። 😎 የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከርና ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተክህነት እንዲኖረን ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን። 9) ጥላቻን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፋ፣ ጥላቻን ከሚያበዛና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲቆጠቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትንም እናወግዛለን። 10) የገጠመን ፈተና ይበልጥ ውስጣችንን ለመፈተሽ፣ አንድነታችንን ለማጠናከር፣ ወንጌልን የበለጠ ለመስበክና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስፋፋት ለበጎ እንጠቀምበታለን፡፡ በመጨረሻም ፍቅር፣ ይቅርታ እና አንድነት እንዲመጣ የደከማችሁትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን። ዋጋችሁንም እግዚአብሔር እንዲከፍላችሁ እንጸልያለን። EOTC TV

Source: Link to the Post

Leave a Reply