አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2014/15 ሂሳብ አመት ከታክስ በፊት 747.1 ሚሊየን ብር አትርፌያለሁ አለ ።ባንኩ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር አሃዙ የ140 በመቶ ጭማሪ ማ…

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2014/15 ሂሳብ አመት ከታክስ በፊት 747.1 ሚሊየን ብር አትርፌያለሁ አለ ።

ባንኩ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር አሃዙ የ140 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም ገልጿል።

ባንኩ በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ 4.7 ቢሊየን አጠቃላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልፆ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ35 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብሏል ።

የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠን 35.6 ቢሊየን ብር ደርሷል የተባለ ሲሆን ፤ በበጀት አመቱ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 27.3 ቢሊየን ብር መሆኑ ተገልጿል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ለደንበኞቹ የሰጠው የብድር መጠን ከጠቅላላው 75 በመቶ ሲሆን፤ የባንኩ ጠቅላላ የአስቀማጭ ደንበኞች ቁጥር ደግሞ 1.6 ሚሊየን ደርሷል ነው የተባለው። ይህም የ11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል መጠን 2.63 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል።

የባንኩ የታመመ የብድር መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር መሻሻል የታየበት መሆኑም ተነስቷል።

ባንኩ በዛሬው ዕለት 19ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply