You are currently viewing አንቡላንሶች ከተፈለገው አላማ ውጭ አገልግሎት በመስጠታቸው እናቶች በቤታቸው እንዲወልዱ እየተገደዱ መሆኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 19 ቀን 2015…

አንቡላንሶች ከተፈለገው አላማ ውጭ አገልግሎት በመስጠታቸው እናቶች በቤታቸው እንዲወልዱ እየተገደዱ መሆኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2015…

አንቡላንሶች ከተፈለገው አላማ ውጭ አገልግሎት በመስጠታቸው እናቶች በቤታቸው እንዲወልዱ እየተገደዱ መሆኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ከተማዎች ለእናቶች የተመደቡ አንቡላንሶች ከተፈለገው አላማ ውጭ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ እየፈጠረ ስለመሆኑ የገለጹት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያላለም ፈንታሁን ናቸው። አስተዳዳሪው በጻፉት ደብዳቤ እንደገለፁት ተሽከርካሪዎቹን ከተቀጠረ የመንግስት ሹፌር ውጭ ሌሎች ያልተቀጠሩ አሽከርካሪዎች ሲጠቀሙባቸው ታይቷል ብለዋል። ሲቀጥሉም በመንግስት ተቀጥረው መኪናቸው ተበላሽቶ ስራ ፈትተው የተቀመጡ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን ተከትሎ የመልካም አስተዳደር ችግር ተፈጥሯል ብለዋል። ለወላድ እናቶች እንዲያገለግሉ የተመደቡ አንቡላንሶች ከተፈለገው አላማ ውጭ በማገልገላቸው እናቶች በቤት ውስጥ እንዲወልዱ በመሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል ያሉት አስተዳዳሪው በመኪና አጠቃቀም ላይ ክትትል በማያደርጉ አመራሮች እና መኪናውን ለሌላ ላልተቀጠሩ ሹፌሮች አሳልፈው በመስጠት ከወላድ እናት ውጭ ሌላ አገልግሎት እየሰጡ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply