አንዳንድ ወገኖቻችን በማህበራዊ ሚዲያ የሚካሄደውን ዘመቻ ውጤቱን አሳንሶ የማየትና የማናናቅ ነገር አያለሁ! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 17/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ…

አንዳንድ ወገኖቻችን በማህበራዊ ሚዲያ የሚካሄደውን ዘመቻ ውጤቱን አሳንሶ የማየትና የማናናቅ ነገር አያለሁ! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 17/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አንዳንዶቹም መሬት ላይ የወረደ የተግባር ስራ ይሰራ፣ መፍትሄ ፈልጉ ይላሉ። መፍትሄው እንዲሁ መፍትሄ ፈልጉ ተብሎ ለተወሰነ አካል ብቻ የሚገፋ ሳይሆን ሁሉንም የአማራን ባለድራሻዎች ያሳተፈ ውይይትና ክርክር ተደርጎ መላ የሚፈለግለት ውስብስብ ጉዳይ ነው። አቅልሎ መመልከት ወይም መፍትሔ የለውም ተብሎ ተስፋ የሚቆረጥበት ጉዳይም አይደለም። 1) ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚደረገው ዘመቻ ህዝባችንንም ሆነ አለማቀፉን ማህበረሰብ መረጃ የመስጠትና የሀሳብ በጉዳዮቻችን ዙሪያ የጋራ ሀሳብ እንዲኖረን ስለሚያደርግ ተጠናክሮና እንደሰሞኑ ተናቦ መቀጠል አለበት። 2) ከክልሉ ውጪ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች በደህንነት ስጋት ውስጥ የሚኖረውን አማራ በተመለከተ መንግስት ምንም አይነት የደህንነት ዋስትና ሊሰጥ እንደማይችል ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ከበቂ በላይ ተረጋግጧል። ስለዚህ መፍትሔው በአማራ ህዝብ እጅ ላይ ነው ማለት ነው። ምን ይደረግ በሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ዙሪያ ልሂቃንን፣ ፓለቲከኞችን፣ ምሁራንን፣ ወጣቶችን፣ ዳያስፖራውን፣ ጋዜጠኞችንና በደህንነት ስጋት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ያከተቱ ጥልቅ ውይይቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። 3) በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰረታዊ መፍትሔዎችን በመፈለግ መተግበር ካልተቻለ የእገታ ፖለቲካ አራማጆችና ፋሽስት ጨፍጫፊዎቻቸው ለአስርት አመታት በተጋቱት የአማራ ጥላቻቸው ተነስተው እያካሄዱት ያለውን የማያባራ ጭፍጨፋቸውንና የአማራ ፍጅትን ያቆማሉ ተብሎ አይታሰብም። በመፍትሔዎች ዙሪያ የውይይት መነሻ ሀሳቦችን በተለያየ መንገድ ለማቅረብ እሞክራለሁ። በመፍትሔዎች ዙሪያም በየአካቢቢያችንና በዙሪያችን ውይይት የምንጀምርበት ጊዜው አሁን ነው። © ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply