You are currently viewing አንዳንድ ወገኖች በፋኖ ላይ ከምትሰጡት እኩይ አስተያየት ፣ስም የማጠልሸት ፣ ኢ-ፍትሃዊ  ፍረጃ እና ከእምነትና ከፖለቲካ ተቋም ጋር ከማዛመድ እንድትታቀቡ ሲል የአማራ ፋኖ በባህርዳር አሳሰበ…

አንዳንድ ወገኖች በፋኖ ላይ ከምትሰጡት እኩይ አስተያየት ፣ስም የማጠልሸት ፣ ኢ-ፍትሃዊ ፍረጃ እና ከእምነትና ከፖለቲካ ተቋም ጋር ከማዛመድ እንድትታቀቡ ሲል የአማራ ፋኖ በባህርዳር አሳሰበ…

አንዳንድ ወገኖች በፋኖ ላይ ከምትሰጡት እኩይ አስተያየት ፣ስም የማጠልሸት ፣ ኢ-ፍትሃዊ ፍረጃ እና ከእምነትና ከፖለቲካ ተቋም ጋር ከማዛመድ እንድትታቀቡ ሲል የአማራ ፋኖ በባህርዳር አሳሰበ። “ከፋኖ ላይ እጃችሁን አንሱ!” ያለው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በወቅታዊ ጉዳይ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። በመጀመሪያ በጎንደር ከተማ በተፈጠረ ግጭት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችንን ፈጣሪ ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ ፤ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይስጥልን እንላለን። በተፈጠረው ግጭት የፖለቲካ ትርፍ ለመስራት ፣ክልሉን የግጭት ማዕከል ለማድረግ እና አማራን ህዝብ ሁለንተናዊ እረፍት ለመነሳት የምታደረጉትን እንቅስቃሴ በፅኑ እንቃወማለን ። የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በፋኖ ላይ ከአንዳንድ ወገኖች እየተሰጠ ያለውን ፍርደ ገምድል አስተያየትና ፍረጃ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በፅኑ ያወግዛል። እንደዚህ ያለ የስም ማጠልሸት እንቅስቃሴ ለምን አላማ እንደሆነ በየትኛዉም አካባቢ የሚገኘው መላው የአማራ ፋኖ ይገነዘባል። “ሊበሏት ያሰቧትን …..” የሚለውን አባባል ማስታወስ ተገቢ ነው። በመሆኑም ሁሉም አማራ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በጥንቃቄና በንቃት መከታተል ይገባል። ፋኖነት የክርስቲያኑም ፣የሙስሊሙም ፣የይሁዲው ወዘተ…. ዋስ ጠበቃ ፥አለኝታ ፥መከታ ነው ። ፋኖነት ለመላው የአማራ ህዝብ ዘብ ፤የህዝባችንን መከራ ከፊት ቀድሞ ራሱን ለመሰዋትነት ያዘጋጀ ፤ህዝብ ሲበደል ፣ፍትሃዊነት ሲጓደል ፤ስርዓት አልበኝነት ሲሰፍን ፤በራሱ ትጥቅና ስንቅ ፤ሀብቴን ፥ንብረቴን ሳይል ፤ልጄ ፥ቤተሰቤን ሳይል ራሱን መሰዕዋት አድርጎ ፍትህ የሚያሰፍን ከህዝብ መካከል የወጣ የህዝብ ልጅ ፤የመላው አማራ ህዝብ አለኝታ ነው ። በመሆኑም አንዳንድ ወገኖች በፋኖ ላይ ከምትሰጡት እኩይ አስተያየት ፣ስም የማጠልሸት ፣ ኢ-ፍትሃዊ ፍረጃ እና ከእምነትና ከፖለቲካ ተቋም ጋር ከማዛመድ እንድትታቀቡ በማለት የአማራ ፋኖ በባህርዳር ጥሪውን ያስተላልፋል። ፋኖ የመላው አማራ ህዝብ አለኝታ ነው! ፋኖ የአማራ ህዝብ ህልውና ጠበቃ ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply