
#አንድ ሁኑ እና አንድ አድርጉን! የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ብልጽግና በዘመነ ካሴ ነፃነት ላይ የጋራ ፖለቲካዊ አቋም ሊኖራችሁ የግድ ይላል። ያለበለዚያ የህዝባችን ምልክት የሆነውን ዘሜን አስራችሁ በፍፁም የተደቀነባችሁን የአብይ አህመድን ሴራ በድል አትወጡም። ዛሬ አብይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ ከጌታቸው ረዳ እና ታደሰ ወረደ ጋር በአራት ኪሎ እና ደብረ ዘይት በአማራው ለይ እየቆመሩ እኛ ግን እርስ በእርሳችን እየተበላላን ድሮም ስንጥር ያለበትን የአማራ አንድነት የበለጠ እያዳከምን የመከራ ዘመናችንን እናረዝማለን። “የመዳን ቀን ዛሬ ነው” እንዲል መጽሃፍ ቅዱስ፣ ብአዴን/የአማራ ብልጽግና የሚድነበት ትክክለኛ ወቅት አሁን ነው። በተወሰነ መልኩም የአማራ ክልል መንግስት አሁን ላይ ጥሩ ጥንካሬ እያሳየ እንደሆነ ከክቡር ፕሬዚዳንቱ ይልቃል ከፋለ (PhD) አንደበት እየሰማን ነው። ይህ ጥንካሬ ወደ ታች የወረደ ማደራጀት፣ ህዝብን ሞብላይዝ ማድረግ እና ወደ ተቋማዊ ትግበራ ቢቀየር ደግሞ የሚሳለቁብን ይቅርታ የሚጠይቁበት ቀን እሩቅ አይሆንም። ለዚህ ግን ህዝብን ወደ አንድ አስተሳሰብ ማምጣት፣ ባይቻል እንኳን ወደ ማግባባት መምጣት የግድ ነው። በዚህ መሰረት እኛን አንድ አድርጋችሁ ከህዝብ ጎን የምትሆኑበት፣ ህዝቡም ከጎናችሁ የሚሆንበት ወቅት አሁን ነው። ህዝብ የሌለው ትግላችሁ ባዶ ይሆናል። እኛ ደግሞ በዚህ ሰዓት ቅድሚያ የምንሰጠው ለልጃችን ነው። ልጃችን አርበኛ ዘመነ ካሴ በተለያየ የሀሰት ክስ ቢከሰስም ፍ/ቤት ግን ነፃ ብሎታል። ዘመነ ካሴ የፖለቲካ እስረኛ እንጅ ወንጀለኛ እንዳልሆነ መላው ፍ/ቤትም ህዝባችንም እናውቃለን። “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥ ነች፣ ባንዲራዋ የኦርቶዶክስ ነው፣ አማራ ከኦሮምያ ምድር መፅዳት አለበት….” እያለ አማራውን ያስጨፈጨፈ የኦነግ ሰው አመራርና ሚኒስቴር በሚሆንባት ኢትዮጵያ …የመናገር ነፃነቱን ተጠቅሞ በተደገጋሚ “የአማራው ግድያ እና ጭፍጨፋ ይቁም!” የሚል ዘመነ ካሴን እስር ቤት አስራችሁ ታሰቃየላችሁ??? ባስቸኳይ ልጃችንን ፍቱልን © እንዳላማው ክንዴ ባህር ዳር #freezemenekassie #FreeAllFano cc Yilkal Kefale-ይልቃል ከፋለ (PhD) Semma Tiruneh_ሰማ ጥሩነህ (PhD) Girma Yeshitila Getachew Jember (PhD) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post