
ከ30 ዓመታት በፊት ወደ ሶቪየት ኅብረት ለትምህርት የሄዱት አቶ ተፈራ የኋላ የኃያሏ አገር ህልውና አክትሞ ቦታዋን ሩሲያ ስትይ እዚያው ነበሩ። ሩሲያን አገሬ ብለው ትዳር መስርተው ልጆች አፍርተው የአገሪቱ ዜጋ ቢሆኑም ኢትዮጵያ ከውስጣቸው አልወጣችም። የዛሬ ዓመት ጦርነቱ ሲጀመር አስፈላጊ ከሆነ ለአባት አገር ሩሲያ ተሰልፈው ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ነግረውን ነበር። ዛሬ ከዓመት በኋላ ስላለው ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።
Source: Link to the Post