አንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጨረቃ ላይ መንኮራኩር በማሳረፍ የመጀመሪያው የንግድ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠራ።ሂውስተን መቀጫውን ያደረገው ኢንትዩቲቭ ማሽንስ ኦዲሴየስ የተሰኘውን ሮቦት በጨረቃ ደቡብ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/azS6gTn6H_ZX0eygDcF7vlKw8LevlVyLlKmrlXBmJSxPPZgou3LjgWGUEGq91s1yUSL-OIuYHxG6kq6POhEmqMkw1ns1uCfJHBNPNzs6T5T-OS2LxBAi_jdXt6zpJ29ySNWsalOX_EYtfHLZ1VjJnrIDwCKbg9fsFI1x3H9IOkwCVhu3UHcthQzT7e6_TU9U63GogN_-6Zta713zud2wyZqjRtomecBZWTL3TcvUIiUU5oMbpq0cUsvc-27FdlpfNiEm92ce50xtsErWd9DW31PhAeqGvwmoiUVmFqgUJJNhpaQ4CvPNVnyk_AmHxqiPMWR9RhXujnP_htjYueEmjg.jpg

አንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጨረቃ ላይ መንኮራኩር በማሳረፍ የመጀመሪያው የንግድ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠራ።

ሂውስተን መቀጫውን ያደረገው ኢንትዩቲቭ ማሽንስ ኦዲሴየስ የተሰኘውን ሮቦት በጨረቃ ደቡብ አቅጣጫ አሳርፏል።

ሮቦቱ ማረፉን ለማረጋገጥ ተቆጣጣሪዎች ጥቂት ደቂቃዎችን ቢወስድባቸውም የማታ ማታ መልዕክት አግኝተዋል።

የበረራ ዳይሬክተሩ ቲም ክራይን “እኛ የምናረጋግጠው ያለ ጥርጥር መሳሪያዎቻችን በጨረቃ ላይ መሆናቸውን እና መረጃ እያስተላለፍን መሆኑን ነው” ብለዋል።

ዜናውን ተከትሎ የኩባንያው ሠራተኞች ደስታቸውን በጭብጨባ ገልጸዋል።

ዜናው ለንግድ ኩባንያዎች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአሜሪካ የጠፈር ፕሮግራምም መሰረታዊ ነው ተብሏል።

ኢንትዩቲቭ ማሽንስ የአሜሪካን የግማሽ ምዕተ ዓመት ከጨረቃ ውጭ የመሆን ታሪክ ቀይሮታል።

የአሜሪካ ንብረት በጨረቃ ላይ ያረፈው በአውሮፓውያኑ 1977 በመጨረሻው የአፖሎ ተልዕኮ ወቅት ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply