አንድ ግለሰብ የሴል ስር ንቅለ ተከላ ከተደረገለት በኋላ ከኤች አይ ቪ በሽታ መዳን መቻሉ ተረጋገጠ፡፡
በጀርመን ዱሰልዶርፍ ከተማ የሚኖረዉ የ53 ዓመት ግለሰብ ለ10 ዓመታት ያህል ከኤች አይ ቪ ቫይረስ ይኖር ነበር፡፡
10 ዓመት ከቫይረሱ ጋር የኖረዉ ይህ ግለሰብ የሴል ስር ንቅለ ተከላ ከተደረገለት በኋላ ከቫይረሱ መዳኑ መረጋገጡን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ግለሰቡ ለአራት ዓመታት የኤች አይ ቪ ቫይረስ መከላከያ መድሀኒቱን እንዳልወሰደ እና በሽታዉ ድጋሚ እንዳልታየበት መረጋገጡንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡
በእስከዳር ግርማ
የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረሃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።