You are currently viewing << ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ የተጠመደ ፈንጅ ነው! >>  // አንጋፋው ፖለቲከኛ – ልደቱ አያሌው// መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን የገጠማቸው ሀገርን…

<< ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ የተጠመደ ፈንጅ ነው! >> // አንጋፋው ፖለቲከኛ – ልደቱ አያሌው// መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን የገጠማቸው ሀገርን…

<< ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ የተጠመደ ፈንጅ ነው! >> // አንጋፋው ፖለቲከኛ – ልደቱ አያሌው// መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን የገጠማቸው ሀገርንና ህዝብን እየገደለ ያለው አደገኛ የናርሲስቲክ (Narcissistic) የስብዕና መዛነፍ ህመማቸው! << ...እኛን ጨምሮ አለምን የሚያምሷት እነዚህ የስብዕና መዛነፍ ችግር ያለባቸው ግለሠቦች በመሪነት እየተቀመጡ ነው! >> እንደ የስነ-ልቦና ፥ የስነ-አዕምሪና የባህሪየ-ሠብ ጠበብቶች የጥናት ውጤቶችና ግኝቶች ፥ የሠው ልጅ የስብዕና መዛነፍ አዕምሯዊ ህመም ፥ ከግለሠባዊ ህይወታችን እስከ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ምስቅልቅሎች የሚያደርስ ውጤትን ያስከትላል፡፡ በተፈጥሮና በሠው ሠራሽ ችግሮች የሚከሰቱት እነዚህ የስብዕና መዛነፎች ማንነታችንና ድርጊታችንን የመቀየር ሀይል አላቸው፡፡ ከነዚህ የስብዕና መዛነፎች ውስጥ ደግሞ Sychopath , SocioPath እና Narcissist ዋናዋናዎቹ የስብዕና መዛነፎች መሆናቸውን ልህቃኑ ያስረዳሉ፡፡ እንደአዶልፍ ሂትለር ያሉት የሳይኮፓዝ ( Sychopathic ) ስብዕና ባለቤቶች እጅግ ጨካኝ ፣ ለፈፀሙት ነገር የማይፀፀቱ ፥ ይቅርታና ርህራሄ ማድረግን ፈፅሞውኑ የማያውቁ ፣ እነሱ እያደረጉት ያለው ድርጊት ብቻ ትክክል መስሎ የሚሠማቸው በድንገት ወደ አውሬያዊ ባህሪ የሚቀየሩ ፥….. አደገኛ የስብዕና ባለቤት ሆነው የምናገኛቸው ከዚሁ ተፈጥሯዊ የስብዕና መዛነፍ ችግራቸው በመነሳት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የናርሲሲስቲክ የባህርይ ችግር / Narcissistic personality disorder ተጠቂ መሆናቸውን ከሚያሳዩት ባህሪና ከሚናገሩት ንግግር ተነስቶ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ህመም አንድ ሰው ራሱን ከፍ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ የጤና እክል ነው። የናርሲሲስቲክ የባሕርይ ችግር በአብዛኛው በወንዶች ዘንድ በጣም የተለመደ ነው ። መንስኤው ባይታወቅም በጄኔቲክና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች የተዋሃደ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ከሚያሳዩት የተለመዱ የሕመም ምልክቶች መካከል ፦ ራስን ልዩና የሁሉ የበላይ ንጉስ አድርጎ የመቁጠር (ግርማዊነት) ፥ ደንታ ቢስነትና ስሜታዊነት፣ የሌሎችን ስሜት ችላ ማለት፣ ከመጠን በላይ አድናቆትን የመፈለግና ትችትን ወይም ነቀፌታን የመፍራት እንዲሁም መቋቋም ያለመቻል ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡ ፍፁም ራስወዳድና አስመሳዮች ናቸው፡፡ የሚያስጨንቃቸው የክብርና የውዳሴ ፍላጎታቸውን ማርካት ብቻ እንጂ ስለሌላው ደንታቢስ ናቸው፡፡ ” ከሁሉም የበለጥኩና የተሻልኩ ነኝ” ብለው ስለሚያስቡ ራሳቸውን ከሌሎች የመነጠል አባዜም የተጠናወታቸው ናቸው፡፡ ከአለም ታላላቅ መሪዎች መካከል አዶልፍ ሂትለር ፥ ፍራንክሊን ሮዝቬልት ፣ ሙሐመድ ጋዳፊ ፣ ፖል ፖት ፥ ስታሊንን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አንባገነናዊ መሪዎች የዚህ ህመም ተጠቂዎች እንደነበሩ ይገለፃል፡፡ እኛን ጨምሮ አለምን የሚያምሷት እነዚህ የስብዕና መዛነፍ ችግር ያለባቸው ግለሠቦች በመሪነት እየተቀመጡ ነው! የዚህ ህመም ተጠቂዎች ህመማቸውን ተረድቶ ወደህክምና ካልተወሰዱ በስተቀር የሚያደርጉት ፣ የሚናገሩትና የሚወስኑት ሁሉ ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ እንደሆነ ስለሚያስቡ አጠናክረው ይገፉበታል እንጂ አይታረሙም ፥ ሌላው ሰው ቢንጫጫና ቢጮህ ለእነዚህ ታማሚዎች ደንታቸው አይደለም፡፡ የሚፈልጉትን ውዳሴና ክብር ከሚያገኙበት መድረክ ፊት እንቅፋት የሚሆንን ሁሉ ያስወግዱታል እንጂ አይራሩለትም፡፡ በሽታው በባለሙያ ምርመራ ተደርጎ ተከታታይና ለረዥም ጊዜ የሚከወን የህክምና ሂደትን ይፈልጋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ወደስልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ የዚህ የበሽታ ምልክቶች የሚስተዋሉባቸው ሲሆን ከጊዜ ወደጊዜም እየተባባሰ መጥቶ “እመራታለሁ” ያሏትን ሀገር ወደፍርስራሽነት እየቀየሯት እንዲሄዱ ብሎም ህዝቡን ወደ አስከፊ የመከራ አዘቅት ውስጥ እንድንዘፈቅ እያደረገን ይገኛል፡፡ አሁንም ቢሆን መላው ህዝባችን በተለይ ደግሞ የፓርቲ ጓዶቹና ቁጭ ብድግ የሚያሰኛቸው ፖፔት ሚኒስተሮቹ ሠውዬ ያለበትን አደገኛ የአዕምሮ ህመም በአንክሮ በመረዳት ፥ በጣም ሳይረፍድ ከህዝብ ስልጣን ላይ ገለል ካልተደረገ ፥ እመኑኝ! ይቺን ሀገር እየተጨበጨበለት አፈራርሷት ፥ እኛንም ከሶሪያውያን የከፋ እጣፋንታን አላብሶን እንዲቀር እድል እየሰጠነው ነው! ሀገርን ለህመምተኛ መጫወቻ ማድረግ ድርብ ድርብርብ ተጠያቂነት የሚያስከትልና ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት ነው ! “ሳይቃጠል በቅጠል” እላለሁ! ሰሚና መላሽ ባያገኙም ፥ ታሪክ ሁሉንም መዝግቧቸው አልፏል…! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply