አኖ ከተማ ውስጥ 60 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/06a20000-0aff-0242-27c8-08db0a173020_tv_w800_h450.jpg

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ “አኖ” በተባለች ከተማ ባለፈው ሳምንት ነዋሪዎቹ “ኦነግ ሸኔ” ብለው የጠሯቸው ታጣቂዎች በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የከተማው ነዋሪዎችና የሟች ቤተሰቦች ተናገሩ።

የጎቡ ሰዮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ባህሩ ኦላና “ኦነግ ሸኔ” ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂዎች ከተማዋ ውስጥ ገብተው 60 ሰዎችን ገድለው፣ ከተማችንን በመክበብ የመንግሥትና የኅብረተሰቡን ንብረት ዘርፈዋል፤ አቃጥለዋል” ብለዋል።

ከክልሉ ባልሥልጣን መስሪያ ቤት ተወክለው በቦታው የነበሩ አንድ ባለሥልጣን ከእነ አሽከርካሪያቸው፣ ጸጥታ አስከባሪ አካላትና ከወረዳው አመራሮች መካከልም ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ጨምረው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና “ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድኖች ቃል አቀባይ ከቨርጂኒያ በሰጡት ምላሽ በተጠቀሰው ዕለትና ቦታ ጥቃት ማድረሳቸውን አምነው “የገደልነው ግን በካምፕ ውስጥ ሲሰልጥኑ የነበሩ የአማራ ኃይሎች ነው” ብለዋል።

የአሜሪካ ድምፅ በስፍራው በአካል ተገኝቶ ካነጋገራቸው ልጆቻቸው የተገደለባቸው እናት፤ “ሸኔዎች” ናቸው ያሏቸው

ታጣቂዎች ቤታቸው ገብተው ሁለት ወንድ ልጆቻቸውን ገድለው ሴት ልጃቸውንም እንዳቆሰሉባቸው ተናግረዋል።

ሰሞኑን ወደ ጎቡ ሰዮ አኖ ከተማ ያቀናው ዘጋቢያችን ናኮር መልካ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply