አካባቢዉ ሙሉ በሙሉ ከትሕነግ ርዝራዥ ባለመጽዳቱ ለማደራጀት መቸገራቸዉን የምስራቅ ጠለምት ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ተናገሩ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2013…

አካባቢዉ ሙሉ በሙሉ ከትሕነግ ርዝራዥ ባለመጽዳቱ ለማደራጀት መቸገራቸዉን የምስራቅ ጠለምት ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ተናገሩ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ ጠለምት ወረዳ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር በምስራቁ የጠለምት አቅጣጫ ከክልል (ከባህር ዳር) 465 ኪሎ ሜትር፤ ከዞን (ከደባርቅ) ደግሞ 193 ኪሎ ሜትር ርቅት 12 ቀበሌዎችን አቅፎ ከተከዜ አፋፍ ዲማ ላይ ተመስርቷል፡፡ ምንም እንኳን የወረዳዉ ሁሉም ቀበሌዎች ከርዝራዡ ቡድን የጸዱ ባይሆንም፤ በወረዳዉ የተደራጀዉ አዲስ ጊዜያዊ አስተዳደር ለድጋፍ ከተላኩ የዞን፣ የአጎራባች ወረዳ አመራሮች እና ከኮማንድ ፖስት አባላት ጋር በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በወረዳዉ ደገብራይ፣ አምሾ ምድርና ሜዳ ስላሴ የተባሉ ቀበሌዎች ያልጸዱ ናቸዉ፡፡ ኦፕሬሽኑ በቅርብ ይጠናቀቃል ብለን ብናስብም ቦታዉ አስቸጋሪ በመሆኑ በታቀደለት ጊዜ ማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ በዚህም ህዎሃት ሰርቶ ራስን ከመቻል ይልቅ የእርሱን የእርዳታ እጅ እንዲያማትሩ ያደረጋቸዉ የአካባቢዉ ህዝቦች ለከፋ ችግር ተዳርገዋል፡፡ ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ከልዩ ልዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ ወደ ትዉልድ ቀያቸዉ የተመለሱት ከ25 ሽህ በላይ ተፈናቃዮች ደግሞ የመንግስትን እጅ በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደሚሹም የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታላይ ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ አብርሃም ገለጻ ነጻ በወጡት ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰን በሰራነዉ የማደራጀትና የህዝብ ግንኙነት ስራ ዉጤታማ ሁነናል፤ የአካባቢዉን ዴሞግራፊ በማስተካከልም አማራነታችንን አረጋግጠናል፤ በቀጣይም በድጋፍ ሰልፍ ስሜታችንን እንገልጻለን፤ ባሉት ዉስን አመራሮች ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል፤ የትራንስፖርት፣ የዉሃ፣ እና መሰል አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ እየተሰጡ ነዉ፡፡ ከ70 በመቶ በላይ ትህነግ በጉልበት አስታጥቋቸዉ የነበሩ የግልና የቡድን መሳሪያዎችን አስፈትተናል፤ በተመሳሳይ የራሳችንን ታማኝ የአማራ ሚሊሻ የተሃድሶ ስልጠና በማሰልጠን ላይ ነን፤ በየቀበሌዉም የሰላም አስከባሪዎችን መልምለናል፤ እነዚህ አባላትም አካባቢዉን በሚያዉቁት ሰላም ለማስከበርና ርዝራዡን ለማጽዳት ዝግጁ አድርገናል፡፡ ይሁን እንጅ አዲስ አስተዳደር እንደመሆኑ መጠን በርካታ የአቅርቦት ችግር አለበት፡፡ ከነዚህም መካከል፡- የተሸከርካሪ እጥረት፣ የመንግስት ሰራተኞች ደመዎዝ አለመከፈል፣ የስልክና የመብራት መጥፋት /መቋረጥ፣ የቢሮ ኪራይ ጥበት መኖር፣ ማህተም አለመቀረጹ እና መሰል ችግሮች ተደራርበዉ የፈለግነዉን ያህል አገልግሎት ለመስጠት፣ ዉጤት ለማምጣትና ድል ለመቀዳጀት እንቅፋት ሆኖብናል፡፡ ችግሩን ለማቃለል የሚመለከታቸዉ የዞን፣ የክልልና የፌደራል እንዲሁም ሌሎች የእርዳታ ድርጅት አጋርና ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊዉን ሁሉ በማሟላት የአካባቢዉን ህዝብ የመታደግና ጁንታዉንም ሙሉ በሙሉ ለማጽዳት በሚደረገዉ ርብርብ የበኩላቸዉን እንዲዎጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply