አወዛጋቢ የነበረው የአብን ስብሰባ መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል መጋቢት 12 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ… ፓርቲው ራሱን አድሶ የህልውና አደጋውን ይቀለብሳል…

አወዛጋቢ የነበረው የአብን ስብሰባ መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል መጋቢት 12 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ… ፓርቲው ራሱን አድሶ የህልውና አደጋውን ይቀለብሳል ተብሎ በብዙዎች የተጠበቀው አወዛጋቢው እና ተጠባቂው ስብሰባ መጠናቀቁን አብን አስታወቀ። ያለወትሮ የብልጽግና ገጽ የአብንን ስብሰባ መጀመር የዘገበበት እንዲሁም የመንግስት አፈ ቀላጤዎች ፋና እና የኢፕድ ‹አብን አዳዲስ ሹመቶችን አጸደቀ ›ብለው የውሸት ዜና መስራታቸውን ይታወሳል። የፓርቲው ህዝብ ግንኙንት ውሸት ነው ሹምሽር አላደረኩም። በፍቃዳቸው የለቀቁትን አመራሮችን ሽግሽግ አድርጌያለሁ ብሏል። የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በፓርቲው ውሳኔ አልተስማማንም፤ የፓርቲው ሊቀመንበርን ጨምሮ ትናንት ማታ በነበረው ስብሰባ ረግጠው ወጥተዋል። ስለሆነም ምርጫ ቦርድ ድጋሚ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያስደርግ የሚጠይቅ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆናቸውን ሰምተናል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የማዕከላዊ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫም 1. የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፈተብንን ጦርነት ለመከላከል ያደረግነውን የህልውና ዘመቻ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን 2. ማዕከላዊ ኮሚቴው በድርጅቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ተዘጋጅቶ በቀረበለት በንቅናቄው የ5 ዓመት ስትራቴጂክ አቅድ ላይ በጥልቀት በመወያየትና የማሻሻያ ሀሳቦችን በማካተት ማጽደቁን 3. መሠረት በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የደህንነት ስጋት አሳሳቢ መሆኑን በመገምገም አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻውና መንግሥት በዚህ ረገድ ተቀዳሚ ሃላፊነቱን እንዲወጣ በተጨማሪም በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ከተማሪዎችና ወላጆች አልፎ የማህበረሰባችን ጥያቄ በመሆኑ አገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅትና ትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡት ማሳሰቡን 4. ማ/ኮሚቴው በንቅናቄው የመዋቅራዊና የአሰራር ቁመናውንም 1) አቶ የሱፍ ኢብራሒም – ም/ሊቀመንበርነታቸውን ለቅቀው– የህግና ስነ–ምግባር ጉዳዮች ኃላፊ 2) አቶ አዲሱ ሐረገወይን – የፖሊሲና ስትራቴጂ ኃላፊነታቸውን ለቅቀው ለአቶ ክርስቲያን ታደለ አስረክበዋል 3) አቶ መልካሙ ጸጋየ – የማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው ማዕከላዊ ኮሚቴው መርምሮ ተቀብሎ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን እንደገና አደራጅቶታል። አዲሱ አስፈፃሚም፦ 1) ዶ/ር በለጠ ሞላ – ሊቀመንበር 2) አቶ መልካሙ ሹምዬ – ም/ሊቀመንበር 3) ዶ/ር ቴዎድሮሥ ኃይለማርያም – የማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ 4) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ – የውጭ ጉዳዮችና ዓለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊ 5) አቶ የሱፍ ኢብራሒም የህግና ስነ–ምግባር ጉዳዮች ኃላፊ 6) አቶ ጣሂር መሃመድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ 7) አቶ ጋሻው መርሻ – የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ 8 አቶ ክርስቲያን ታደለ- የፖሊሲና ስትራቴጂ 9) አቶ ሀሳቡ ተስፋው – የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ወስኗል። ፓርቲው ይሄን የመሰለ መግለጫ ቢያወጣም በአሁኑ ወቅት የህልውና አደጋ ለተደቀነበት እና በየቀኑ ለሚታረደው ከክልሉ ውጭ ስላለው አማራ ያለው ነገር አለመኖሩ ብዙዎችን አሳዝኗል። የሁሉም አማራ ማገር ይሆናል ተብሎ የተጠበቀ አብን በወለጋ በምዕራብ ሸዋ በአርሲ እና በመተከል እየሞቱ ስላሉ አማራዎች ምንም አለማለቱ ሁሉም አማራ ለ1አማራ የሚለው መፈክሩ ከቃል ያለፈ እንዳልሆነ ያረጋገጠ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ አማራዎችን ተመልክተናል። አብን የሚስተዋሉ ክፍተቶችን አስተካክሎ ዳግም የአማራ ተስፋ እንደሚሆን የገለጡልንም አልጠፉም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply