አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ።ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተ…

አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ።

ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተመረጡ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ አንዱ ሆኗል።

የምርጥ ባንኮች ልየታ የተደረገው በተለያዩ መስፈርቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የባንኮቹ ትርፋማነት፣ የሀብት ዕድገት፣ተደራሽነት እና የመሳሰሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የተካተቱ ናቸው።

በዚህ መሠረት አዋሽ ባንክ ከ36 አገራት ከተመረጡ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ባንክ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል።

በዚህኛው አመት በተካሄደው ምርጫ ከ1መቶ50 በላይ አገራት የሚሰሩ ባንኮች የተካተቱበት መሆኑም ነው የተገለጸው።

አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ9መቶ38 በላይ ቅርንጫፎች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከ12.1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችንም ማፍራቱ ተነግሯል።

የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ2መቶ15 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል።

ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከብር 1መቶ78 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ለባንኩ የሚሰጠው ዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ዲሲ በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት ጉባኤ ወቅት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply