You are currently viewing አዋሽ ካርጎ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለማዘመን  የሚያስችል ስራ ለመስራት ከመንግስት ጋር ተፈራረመ

አዋሽ ካርጎ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል ስራ ለመስራት ከመንግስት ጋር ተፈራረመ

በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና በአዋሽ ካርጎ ራይድ መካከል በባቡር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ዘርፋአሁን ያለውን መሰረተ ልማት በመጠቀም አገልግሎት ለመስጠትና አብሮ ለመስራት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት መግባቢያ ሠነድ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም መፈራረማቸውን ለፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው ስምምነቱ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት የተሸለ አሰራርና አገልግሎት ለማምጣት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመው ከሃገር ውስጥ ተቋም ጋር በጋራ መስራት የሃገሪቱን የስራ አጥነት ችግርን በመቅረፍ ረገድም ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የአዋሽ ካርጎ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ለሚ ቱጆ በበኩላቸው ድርጅታቸው በጭነት አገልግሎት ያለውን ልምድ በመጠቀም በባቡር ዘርፍ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ባቀረበው መሠረት ኮርፖሬሽኑ በጋራ ለመስራት ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀው መሠረተ ልማቱን በመጠቀም የሃገሪቱ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ተቋማቸው የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል፡፡
በኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ዳይሬክትር የሆኑት አቶ ካሳሁን ሙላቱ ኮርፖሬሽኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 141/2000 የተሰጠው ተልዕኮ በዋናነት የባቡሩ መሠረተ ልማት በሃገሪቷ ውስጥ በመገንባትና በማስፋፋት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሃገሪቷን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ማሳለጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ አግባብ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር እና ሰበታ መኤሶ-ደወንሌ ባቡር መስመሮች ግንባታ ተጠናቆ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሰበታ መኤሶ-ደወንሌ ባቡር መሠረተ ልማት የሚኖረው ሃገራዊ ፋይዳ

ከመነሻው በጥናት ተለይቶ የተቀመጠ ቢሆንም አሁን ላይ እየሰጠ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት በአግባቡ መርምሮ በአዋጭነት ጥናቱ ላይ በተቀመጠው አግባቡ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ ላይ ማድረስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህን ለማድረግ የትራንስፖርት ዘርፉን ችግር በጥናት በመለየት ተገቢውን መፍትሄ መስጠት የሚያስፈልግ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሎጂስቲክስ ስራዎችን በቅንጅት በመስራት የሃገሪቱን የገቢ እና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ የባቡር ትራንስፖርት በገበያው ላይ ያለውን የሎጅስቲክስ ድርሻውን ከፍ ማድረግ አስፈላጊ  መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አቶ ካሳሁን እንደገለፁት ከአዋሽ ካርጎ ጋር የተፈረመውየስምምነት ዋና አላማ  የተገነቡ የባቡር መሠረተ ልማቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም መስጠት የሚችሉትን ከፍተኛውን ጠቀሜታ እንዲሰጡ የሚያስችሉ ህጋዊ አሰራሮችን መሰረት በማድረግ በጋራ ለመስራት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የባቡር አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1048/2009 አንቀፅ 15 መሰረት አንድና ከዛ በላይ የሆኑ የባቡር ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅቶች ፍቃድ አውጥተው በተገነባው የባቡር መሠረተ ልማት ላይ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡበት አግባብን የሚያስቀምጥ በመሆኑ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ አማራጮች ያሉት፤ተደራሽነት ያለውና ሃገራዊ ጠቀሜታው የጎላ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ ከመንግስት እና ከግል ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን ማየት እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አዋሽ ካርጎ ትልቅ ራዕይ ሰንቀው በተነሱ ምሁራን ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ ሎጅስቲክስ ዘርፍ ላይ የተሰማራ የንግድ ድርጅት ሲሆን ከኮርፖሬሽናችን ጋር በመሆን ተገንብተው የተጠናቀቁ የባቡር መሠረተ ልማቶች የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ፤ ተጨማሪ ሃብት ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ በመሳብ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ ለዘርፉ አስፈላጊ የሆኑ የፖሊሲ ድጋፎችንና የአሰራር ማንዋሎችን በጋራ በመለየት እንዲሁም በዘርፉ ውጤታማነት ላይ ተግዳሮት የሆኑ አሰራሮችን በመለየት ለዘርፉ ውጤታማነት በትብብር ለመስራት የተደረገ የመግባቢያ ስምምነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዋሽ ካርጎ በጭነት አገልግሎት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለውሲሆን
በሀገራችን ውስጥ ከሃያ በላይ የደረቅ ወደብ ግንባታዎችንለማከናወን እንቅስቃሴ ጀምሯል።

The post አዋሽ ካርጎ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል ስራ ለመስራት ከመንግስት ጋር ተፈራረመ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply