አየርላንድ እስራኤል በፍልስጤም ላደረሰችው ውድመት ካሳ እንድትከፍል ጠየቀች፡፡የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እስራኤል በፍልስጤም የሚገኙ እና በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ ተቋማትን ስላ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/dqfGfkdHNgXCOdon-wk3YyP1h-tadCjs3E5h-QYLvGrdHGcGzDPV_M68OKklnZgMbDvrrfIokgbbMnuyooVafiSul7li5eTOCq5uI-F8VScW9_ljjcPvWadtKYRnO31UntU5Kny23FmQ9RTFb8vbzdG8nprr3YeOigjwc3hWy3TyIdfVcLSAQQC-qdUM9E_dNHkWoBQMCx3qSdx3uvnjLgaaUzNHGP7SANBiFZBLDCuciDHgXEKF1C6QB0CZ9ORpFxRSEMZPwjmdakNBlegllkXiN7ain-HAzXC8fxTWUiye8WdJXM6jc7fPg_glCa3Egivs4Q8MSbkaeNBQbAX7HA.jpg

አየርላንድ እስራኤል በፍልስጤም ላደረሰችው ውድመት ካሳ እንድትከፍል ጠየቀች፡፡

የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እስራኤል በፍልስጤም የሚገኙ እና በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ ተቋማትን ስላወደመች ካሳ ትክፈል ሲሉ ጠይቀዋል።
ማይክል ማርቲን በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቤልጄም ብራስልስ አምርተዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በብራሰልስ ከአይሪሽ ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ” የአውሮፓ ህብረት ለፍልስጤማውያን መሠረተ ልማቶች ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑ እስራኤልን አስቆጥቷል ብለዋል፡፡
ይህንንም መነሻ በማድረግ እስራኤል በተቋማቱ ላይ የምታደርገው የማውደም ተግበር ተቀባይነት የለውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እስራኤል በተቋማቱ ላይ እያደረሰች ባለው ጥቃት የተነሳ በርካታ ዜጎች ካሉበት ቦታ እየተፈናቀሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህም ከሰብሃዊነት እሴቶች አንጻር በአለም ማህበረሰብ ዘንድ ምንም ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ቀስቃሽ ነው በማለት የአየርላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አብራርተዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply