You are currently viewing #አይዞሽ_አታልቅሺ አይዞሽ አታልቅሺ እምየ እናታለም ፣ ምንም የተለየ አዲስ ነገር የለም ፣ ለሀይማኖት መሞት ውርደት እኮ አደለም ፣… ቀድሞ አሳይቶናል ጌታ መድሀኒዓለም ። የሩቅ መንገድ…

#አይዞሽ_አታልቅሺ አይዞሽ አታልቅሺ እምየ እናታለም ፣ ምንም የተለየ አዲስ ነገር የለም ፣ ለሀይማኖት መሞት ውርደት እኮ አደለም ፣… ቀድሞ አሳይቶናል ጌታ መድሀኒዓለም ። የሩቅ መንገድ…

#አይዞሽ_አታልቅሺ አይዞሽ አታልቅሺ እምየ እናታለም ፣ ምንም የተለየ አዲስ ነገር የለም ፣ ለሀይማኖት መሞት ውርደት እኮ አደለም ፣… ቀድሞ አሳይቶናል ጌታ መድሀኒዓለም ። የሩቅ መንገድ ተጓዥ ቅርብ አዳሪ ሆኘ ፣ ቀረሁኝ ከመንገድ ባውሬወች ታፍኜ። አትዘኝ አታልቅሽ እምየ በርችልኝ፣ ፍፁም አትከፊ እንዳውም ኩሪብኝ ፣ በሀይማኖት እንጅ በሌላ አልመጡብኝ ። ቀጠሮ ኖሮብኝ ከፈጣሪ ጋራ ፣ ሔድኩኝ ሳልከፍልላት የምየን አደራ ። ፅናቱን ያድልሽ እምየ እናቴ ፣ እምባሽን ያብሠው የሠማይ አባቴ ። በርችልኝ እናቴ ብየሽ ልሠናበት ፣ ተመርጣለች ነፍሴ ለሠማዕትነት ። ዳዊት ተመስገን አዲስ አበባ

Source: Link to the Post

Leave a Reply