You are currently viewing ‹‹አይደገምም››  የተባለው ሲደገም! አሳዬ ደርቤ ➔ህውሓት የተባለው የቀድሞ ድርጅታችሁ ድክመቱን የሚነግሩትን የተቃውሞ ድምጾችን እያፈነ እንደ ዋልታ፣ ኢቲቪና፣ ፋና ያሉ የገደል ማሚቶዎችን…

‹‹አይደገምም›› የተባለው ሲደገም! አሳዬ ደርቤ ➔ህውሓት የተባለው የቀድሞ ድርጅታችሁ ድክመቱን የሚነግሩትን የተቃውሞ ድምጾችን እያፈነ እንደ ዋልታ፣ ኢቲቪና፣ ፋና ያሉ የገደል ማሚቶዎችን…

‹‹አይደገምም›› የተባለው ሲደገም! አሳዬ ደርቤ ➔ህውሓት የተባለው የቀድሞ ድርጅታችሁ ድክመቱን የሚነግሩትን የተቃውሞ ድምጾችን እያፈነ እንደ ዋልታ፣ ኢቲቪና፣ ፋና ያሉ የገደል ማሚቶዎችን ከፍቶ የእራሱን ድምጽ እያዳመጠ ‹‹ጠንካራ ነኝ›› ይል ነበር፡፡ ➔ከዘጠና ሰባቱ ምርጫ ጋር አብረው የመጡ ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን ከሕትመት ውጭ ካደረገ በኋላ የሞደሊስቶችን እና የአርቲስቶችን የምግብ ምርጫ ለሕዝብ የሚያሳዉቁ መናኛ መጽሔቶችን ስፖንሰር ያደርግ ነበር፡፡ ➔የሚተቹትን ጸሐፊዎች እና ጋዜጠኞች ወደ እስር ቤት አስገብቶ በብዕር ሥም እየጻፈ እራሱን በእራሱ ያንቆለጳጵሰው ነበረ፡፡ ➔ከዚህ ባለፈም የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ እልፍ አእላፍ ወጣቶችን አፍሶ ወደ አዋሽ አርባ የማጎሪያ ካምፕ ካስገባ በኋላ ‹‹መለስ አልሞተም፣ ሕገ-መንግሥቱ አይደፈርም›› የሚል ሥልጠና ሲግታቸውና ‹‹አይደገምም›› የሚል ጽሑፍ ያለበት ቲሸርት አልብሶ ሲያስመርቃቸው ነበረ፡፡ ያ ሁሉ የመብት አፈና ግን እንቢተኛ ወጣትን እና አፈንጋጭ ቡድኖችን ከማፍራት ባለፈ አልጠቀመውም፡፡ በመሆኑም ከእለታት ባንዱ ቀን ወጣቶችን የሚያፍንበትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግብሮ፣ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የሚያስተላልፉ ዲሾችን የሚነቅል ኮማንድ ፖስት አዋቅሮ እንዲሁም እነ ኢቲቪን የሚከታተል ትውልድ እፈጥራለሁ ብሎ ጣሪያ ላይ ሲንደፈደፍ ከከረመ በኋላ ወደ ምድር ሲወርድ አራት ኪሎ አካባቢ ያስቀመጠው ወንበር ጠፋው፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ከቦሌ ወደ መቀሌ ተሸኝቶ በአየር መንገድ ፈንታ በጋሪ ሲሄድ እራሱን አገኘው፡፡ የሚገርመው ነገር ታዲያ ታሪክ እራሱን ይደግማል›› እንደሚባለው የብልጽግና መንግሥትም ህውሓት በወደቀበት የአፈና መንገድ ሕያው ሆኖ ሊኖርበት አስቦ እየዳከረ መሆኑ ነው፡፡ በህውሓት ጊዜ በባሕር ዳር ወጣቶች ላይ የተፈጸመው እልቂት በብልጽግና ዘመን ሲፈጸም ትክክል ሆኖ የሚገኝ ይመስል በረከት ስምዖንን ለእስራት የዳረገውን ጥፋት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትና ባለሥልጣናት እየደገሙት ነው፡፡ ሆኖም ግን ከመከላከያ ጋር ለመሞት የተዘጋጁ ፋኖዎችን ባፈኑበት መዳፍ ሰሜን እዝን ከወጉ አሸባሪዎች ጋር መተቃቀፍ ቢቻልም ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ግን የኋላ ኋላ ውድቀትን እንጂ የዙፋን መርጋትን አያመጣም፡፡ ጥጋባችሁን የሚናገሩ አንደበቶችን ወደ እስር ቤት በመወርወርም መራባቸውን እና እጦታቸውን መናገር የጀመሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፎች ዝም መሰኘት አይቻልም፡፡ ችግር ፈጣሪን ታቅፎ ‹‹ሕግ ማስከበር›› በሚል ሥም ‹‹ሕግ ይከበር›› የሚሉ ዜጎችን በማፈን ብሎም ‹‹ሕልውናችን ይጠበቅ›› የሚሉ ፋኖዎችን በማሳደድም ሕገ ወጦችን ማስፋፋት እንጂ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚቻል አይሆንም፡፡ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply