አደረጃጀቶችን በመፈተሽና በማጠናከር የአማራን ሕዝብ የሚመጥን መዋቅር ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር…

አደረጃጀቶችን በመፈተሽና በማጠናከር የአማራን ሕዝብ የሚመጥን መዋቅር ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር…

አደረጃጀቶችን በመፈተሽና በማጠናከር የአማራን ሕዝብ የሚመጥን መዋቅር ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ ጎጃም ዞን የአብን አመራሮች ትላንት ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዞኑ ሥር ከሚገኙ የንቅናቄው የወረዳ ሰብሳቢዎች ጋር በደብረማርቆስ ከተማ የጋራ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በዋናነት የ2013 በጀት ዓመት እቅድ መገምገም፣ የወረዳዎችን ሪፖርት ማዳመጥ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየት ነበር ያሉት የዞኑ የአብን ሰብሳቢ አቶ መልሰው ሉሌ በእቅድ አፈፃፀሙ ላይ እንደ ችግር በቀረቡ ጉዳዮች ላይም በጋራ ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ተናግረዋል። የወረዳና የዞኑ አመራር ተናቦ እቅድ አፈፃፀሙን በጋራ እየገመገመ መስራቱ አመራሩ ወቅቱን ባገናዘበና ሕዝባችንን በሚመጥን መንገድ ሥራዎችን ለማከናወን ይረዳል ያሉት አቶ መልሰው ዞኑ በሥሩ የሚገኙ የወረዳ አደረጃጀቶችን በመፈተሽና በማጠናከር የአማራን ሕዝብ የሚመጥን መዋቅር ለመፍጠር እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል። አብን በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች መዋቅሩን መዘርጋቱንም በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply