አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሐፍት ህትመት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል። የምህራን መምሪያ እና የተማሪዎች መፅሀፍት የህትመት ሥራ ከሚያከናውኑ ድርጅቶች ጋር በተገባው ውል መ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/GsoRqxoJSXUfHagGzWiXklEQCc73jQXb1FWhX_zpWIhfzpEAxhTvhtGAkn7jMZ53nBvKaZ3rrNXJCpKNSNOajdXx-ixSwJOIxmxGs1RU9h2ov3Lz-8TTsLUDL6KzBA0mtv_5FctBFR3GWb6FtAktPILDIkbBgn1TK5C0du3reCzbmO_ezsasdHcFH_Xaebsnqr37qlLzwQlA8KJv-RwZKXK_YNEio7L_jnmscGut4KXgwt5as9fGuzQD61P5KpShco8sN5SdhSr0K-VLIXQawLP__lfcwv_2PPKbopv4UqDdcsnwbL8MU3gOnSSRPo1_LnB0fPktp3toY-G17fMu5A.jpg

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሐፍት ህትመት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የምህራን መምሪያ እና የተማሪዎች መፅሀፍት የህትመት ሥራ ከሚያከናውኑ ድርጅቶች ጋር በተገባው ውል መሰረት ህትመቱ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እስከዛ ድረስ መፅሀፍቱ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረጉን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ተናግረዋል።

ዘንድሮ ወደ ትግበራ ለገባው ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁት መፅሀፍት እና የመምህራን መምሪያ ህትመት ለነባሩ ስርዓተ ትምህርት ወጪ ከተደረገው በ57 ሚሊዮን ብር ያነሰ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን
ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply