አዲሱን የክልል አደረጃጀት አልቀበልም—ጋዴፓየጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) አዲሱን የክልል አደረጃጀት እንደማይቀበል ገለፀ።በደቡብ ክልል የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) አዲሱን የክል…

አዲሱን የክልል አደረጃጀት አልቀበልም—ጋዴፓ

የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) አዲሱን የክልል አደረጃጀት እንደማይቀበል ገለፀ።

በደቡብ ክልል የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) አዲሱን የክልል አደረጃጀት እንደማይቀበል የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዳሮት ጉምኣ ተናግረዋል።

ፓርቲው በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከአዲሱ የክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ አቋሙን ገልጿል።

በቅርቡ በመንግስት ውሳኔን አግኝቶ የተደራጀው የደቡብ ምእራብ ክልል ጉዳይ እልባት ቢያገኝም፣ ሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች በፈረሰው የቀድሞ ደቡብ ክልል ውስጥ እንዲቀጥሉ ተደርገዋል።

በህገ-መንግስቱ መሰረት ህዝበ ውሳኔ መደረጉን የተናገሩት የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ዳሮት፣ ህዝቡ መንግስት የወሰነውን አዲሱን የክልል አደረጃጀት ህዝቡ እንደማይቀበል ተናግረዋል።

በመሆኑም በህገመንግስቱ መሰረት የጋሞ ህዝብ በ2011 ዓ.ም ክልል የመሆን ጥያቄ በመንግስት ምላሽ እንዲሰጠው ማንሳቱን አስታውሰዋል።

ነገር ግን መንግስት ህገመንግስቱን ባላከበረና የህዝብን መብት በጣሰ መልኩ ጥያቄውን ችላ ማለቱን ገልፀዋል።

ህገመንግስቱ ላይ ክላስተር የሚባል አሰራር የለም ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር ፣መንግስት እራሱ ህገመንግስቱን እየጣሰ የህዝብ ተፈጥሯዊ ነፃነቱን እየገፋ ነው ሲሉ ተችተዋል።

ይህ ድርጊት ከህገ-መንግስቱ ባለፈ የህዝብን ደህንነት እና በመንግሥት ላይ ያለውን እምነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው ነዉ የተናገሩት።

የክላስተር አደረጃጀቱ የጋሞን ህዝብ ጨምሮ የሌሎች ብሔሮችን ባህል እና እሴት ከማኮሰሱም ባለፈ በህዝብ መካከል ግጭትን አስነስቶ ለእልቂት ሲዳርግ እንደነበርና አሁንም እንደሚቀጥል ሰጋታቸውን ያነሱት ደግሞ የጋሞ መማክርት ማህበር የሽምግልና ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ ሰዲቅ ስሜ ናቸው።

ህዝቡ ማንነቱን እና ባህሉን ማሳደግ ይፈልጋል፤ ስለሆነም የህዝብን ድምፅ በማክበር መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል ሲል ፓርቲዉ አስታዉቋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply