
የ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ያሽመደመዳት ሶማሊያ በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተወጠረች አገር ናት። በዚያ ላይ ስር የሰደደ ሙስና እንዲሁም የጎሳ ክፍፍል ይንጣታል። አክራሪው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ ሶማሊያን ከጥግ ጥግ ከማናጋት አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል። ለመሆኑ የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ መመረጥ ለሶማሊያ፣ ለአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነትስ ሊለወጥ ይችላል?
Source: Link to the Post