አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስር የኮቪድ 19 ስርጭትን ሊቀንሱ የሚችሉ ማሻሻያዎችን ሊፈርሙ ነው፡፡

ከትናንት በስቲያ የኋይት ሃውስ ቁልፍን ከዶናልድ ትራምፕ የተቀበሉት ዲሞክራቱ ባይደን ከትናንት ማለዳ ጀምሮ በቢሮ ስራቸው ላይ ታይተዋል፡፡የ79 ዓመቱ ባይደን በተህዋሲው ክፉኛ የተጎዳችውን ሐገራቸውን ከዚህ ወረርሽኝ ለመታደግ ያግዛል ያሉትን አዳዲስ መመሪያዎች አዘጋጅተዋል፡፡

ቀዳሚው ክትባቱ እንዲፋጠን ማድረግ ነው፡፡ በሁለተኛነት የምርመራ አቅምን ማሳደግና ማፋጠን አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ያተኮሩበት አቅጣጫ ነው፡፡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች በብዛት እንዲመረቱ ትእዛዝ ሰጥተዋል ጆ ባይደን፡፡46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ከትናንት በስቲያ ቃለ መሃል የፈፀሙት ጆ ባይደን እነዚህን ጨምሮ አዲስ አስር ኮቪድ 19ን መመከት የሚያስችሉ መመሪያዎችን አውጥተው ተግባራዊ እንዲደረጉ በፊርማቸው ሊጠይቁ መዘጋጀታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡በመላ ዓለም በዚሁ አደገኛ ቫይረስ ከሞቱ 2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ከ406 ሺ በላዩ አሜሪካውያን መሆናቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል በኩል ባሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ ሲተቹ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

*****************************************************************************

ቀን 14/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ምስል፡- የባይደን

The post አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስር የኮቪድ 19 ስርጭትን ሊቀንሱ የሚችሉ ማሻሻያዎችን ሊፈርሙ ነው፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply