አዲሱ የኤች አይቪ መድሃኒት ውጤታማ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡

ኤች አይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ፡፡

ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነት ውስጥ የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት መረጋገጡ ታውቋል።

የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተውጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው።

በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች እየወሰዱ ይገኛሉ።

ከቼልሲ እና ዌስትሚኒስትር ሆስፒታል ጋር በመሆን የመድኃኒቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተደረገውን ሙከራ የመራው የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ጥናቱ በዓይነቱ ከዚህ ቀደም ከተሰሩ ጥናቶች ሰፊ መሆኑን ገልጿል።

ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2017 እስከ ሐምሌ 2020 ባሉት ጊዜያት እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ 157 የሥነ ተዋልዶ ጤና ተቋማት ላይ ተካሂዷል።

ይህ ጥናት ‘ፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፍላክሲስ (ፒአርኢፒ)’ የተባለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን መድኃኒቱ በኤችአይቪ የመያዝ ዕድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል።

በክሊኒክ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳመለከቱትም መድኃኒቱ 99 በመቶ ውጤታማ ነው።

የዩኬ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲ የመድኃኒቱ ውጤታማ መሆን የአገሪቷ መንግሥት በ2030 የኤችአይቪ ሥርጭትን ዜሮ ለማድረስ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳል ብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply