አዲሱ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኬኒያዉ ፕሬዚዳንት በአዲስአበባ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ የኹለቱን አገራት ትብብር እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊየም ሩቶ በዛሬው ዕለት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በነሀሴ 3/2014 በተካሄደው የኬኒያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ መስከረም ወር ላይ በተከናወነው የፕሬዝዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መገኘታቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸውን ከኢትዮጵያ መጀመራቸውም ታውቋል።

The post አዲሱ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply