አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለኢትዮጵያም ስጋት መሆኑ ተገለጸ፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የአስቸኳይ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ 19 ምላሽ ምክትል አስተባባሪ ዘውዱ አሰፋ ለአሐዱ እንደገለጹት አሁን የተገኘው ቫይረስ እንደሌሎች የአለም ሀገራት ሁሉ ኢትዮጵያንም የሚያሰጋት ነው፡፡ቫይረሱ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ስለመግባቱ የሚያመላክት መረጃ የለም ያሉት አቶ ዘውዱ ህብረተሰቡ ራሱን ከቫይረሱ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከል እርምጃዎችን መውሰዱን እንዲቀጥል አሳስበዋል።ኢትዬጵያን ጨምሮ የተለያዩ የአለም ሀገራት በሮቻቸውን አልዘጉም ያሉት አቶ ዘውዱ ይህ ደግሞ ቫይረሱ በማንኛውም አጋጣሚ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ የሚችልበት እድል ሰፊ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

አዲሱ ዝርያ ወጣቶች ላይ በብዛት መታየቱ አሳሳቢ ያደርገዋልም ተብሏል፤እስካሁን ከእንግሊዝ በተጨማሪ በዴንማርክ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች አገራት መከሰቱን የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው በ70 በመቶ የመሰራጨት እድል እንዳለውም ድርጅቱ ገልጿል።

**************************************************************************

ዘጋቢ፡ሰላም በቀለ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply