አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልል አደረጃጀት የህዝቡን የማንነት ጥያቄ የመለሰ አይደለም—ቁሕዴፓ የቁጫ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)፤አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልል አደረጃጀት የቁጫን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/vlb68BE74LWkJW43wvUSkPJ7lsE00TvWWLCMBMMiDNW3RNCsQf86sFJbB1G7yw-ddDH1vsMmCZPERoYSXvUzJV73B2wXh0nUAV2ViSNMB9akOZVUpdA0ynHNmk0BJjo9geIFlTKSTF7TCxAuPAU_zoCwAGrmf8icBNOoFavECfoD_FCiP17HgBEzgnesKpBWbRGCcCPtKKDuEotIZrhS-QST2nDJqq8XuLfkbI0F587dkAu0hHFhrtwQ6WUrgXDB0pRrIBF9bGF0y6FJw0EP2IawoP2mfoPftJaFVOytXlBXccIT69sCWgzJYwjOrnX5joS8HKLso98AYtINgw5kMA.jpg

አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልል አደረጃጀት የህዝቡን የማንነት ጥያቄ የመለሰ አይደለም—ቁሕዴፓ

የቁጫ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)፤አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልል አደረጃጀት የቁጫን ህዝብ የማንነት ጥያቄ የመለሰ አይደለም ሲል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

የክልል አደረጃጀቱ ከትምህርት ስርዓቱ ጀምሮ የቁጫ ህዝብን በራሱ ቋንቋ የመማር መብትን ያከበረ አይደለም ሲሉ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አቶ በቀለ አበራ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

ህዝቡ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ ቋንቋ የመማር መብቱን አጥብቆ ሲጠይቅ መቆየቱን ያነሱት የፓርቲው ዋና ጸሃፊ፣ ይሁን እንጂ ከፍላጎቱ ውጪ የራሱ ባልሆነ ቋንቋ እንዲማር ተገዷል ብለዋል፡፡

ሰሞኑን ማእከላዊ መቀመጫውን ወላይታ ሶዶ ያደረገው አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለቁጫ ህዝብ አዲስ ተስፋን ይዞ እንደመጣም ፓርቲው አልሸሸገም፡፡
ይሁንና ከክልሉ ህገ-መንግስት ጀምሮ እስከ አደረጃጀቱ ድረስ ምላሽ ሊያገኙ የሚገባቸው ነገሮች በመኖራቸው ፓርቲው አሁንም በትዕግስት እንደሚጠብቅ ገልጿል፡፡

ዛሬም ቢሆን በቁጫ እና በጋሞ ህዝብ መካከል ምንም አይነት ማህበራዊ ችግር እንደሌለ ያነሳው ፓርቲው፣ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ የመንግስት አካላት መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ፓርቲው ሁለቱም ህዝቦች ትላንትም የፖለቲካ ሴረኞችን እኩይ ተግባር እያከሸፉ አብረው ኖረዋል ነግም ይቀጥላሉ በማለት በህዝብ መካከል የሚያቃቅር መሰረታዊ ጉዳይ አለመኖሩን ጠቁሟል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply