
አዲስ መረጃ! ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር አስገብተዋል። ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል። በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ 6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ አስታውቀዋል ። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ አብርሃምም ያቀረቡት ደብዳቤ የቤተክርስቲያን ለዛ ያለበት፣መጸጸትን የሚያመለክት ቢሆን መልካም እንደነበር ገልጸው በቪዲዮ የይቅርታ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እድል እንዲሰጣቸው ያደረጉ ቢሆንም ግለሰቦቹ የተሰጣቸውን ዕድል አልተቀበሉትም ። ምንጭ:- EOTC “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post