“አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እናደርጋታለን ብለው ነበር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር። ቃል በተግባር እየተፈጸመ መሆኑን ትናንት ባደረግነው ጉብኝት አረጋግጠናል። ሰፋፊ ጎዳናዎች፣ ምቹ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ አረንጓዴ አካባቢ፣ ንጹሕና ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የተግባቡና የተዋቡ የግንባታ መልኮች፣ አዲስ አበባን እየቀየሯት ነው።

ቃልን በተግባር ለመቀየር ለተሳተፋ አመራሮች፣ ሌት ተቀን ሳይደክሙ ለፈፀሙ ሙያተኞች እና ሰራተኞች ሁሉ እንዲሁም ይሄን ተግባር በመደገፍ ህንፃቸውን እና መኖሪያቸውን በራሳቸው ተነሳሽነት ላሳመሩ እና ለደገፉ ባለሀብቶች እና ነዋሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል። በሥፍራው የነበረው ሕዝብ በድንገት ወጥቶ ላሳየን ፍቅርና ክብር፣ ለሰጠውም ምስክርነት እናመሠግናለን።” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

Source: Link to the Post

Leave a Reply