አዲስ አበባ በሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ክልላዊ ሰንደቅ ዓላማ መስቀልና ማዘመር የሕግ መሰረት የለውም- ኢሰመኮ

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-f783-08daeaab545f_tv_w800_h450.jpg

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የክልል ሰንደቅ ዓላማን የመስቀል እና ክልላዊ መዝሙርን የማስዘመር እርምጃ የሕግ መሠረት የሌለው ነው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ።

 ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ መሰቀል እና ከክልሉ መዝሙር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የከተማዋ ትምህርት ቤቶች ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የሰንደቅ ዓላማ እና የመዝሙር ጉዳይ ሰበብ ሆነ እንጂ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ችግሩን ለመፍታት መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በተመለከተ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply