አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ባለፈው ሰድስት ወር ውስጥ ምግቦች ላይ በአድ ነገር ጨምረው የተገኙ 18 ተቋማት ላይ እርምጃ ወስጃለው አለ፡፡

ላለፉት ስድስት ወራት በተደረገ የምግብ ቁጥጥር ልክ ባልሆነ መንገድ ሲሸጡ የተገኙ 18 ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ ለጣቢያችን አስታዉቋል፡፡

የባለስልጣኑ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አሰፋ ተሬሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ክስተቶች በተለይ የተለያዩ በአላትን ተገን በማድረግ የሚደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደ አብነትም አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እንዲሁም መርካቶ አካባቢ እርምጃ ከተወስድባቸው አካባቢዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአላት ላይ እንደዚህ አይነት ተግባራት እንደሚበራከቱ በማወቃችን ከመደበኛው ጊዜ በበለጠ በአላት ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረጋልም ብለዋል፡፡

በቀጣይም የዒድ እንዲሁም የፋሲካ በዓላት እየመጡ ስለሆነ ከወዲሁ እቅዳቸው ውስጥ በማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡

ነገር ግን እንደዚህ አይነት ስራዎች የምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ብቻ የሚቆጣጠራቸው ባለመሆኑ የሁሉም ትብብር እና በተለይ የፀጥታ አካላት ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡም በዚህ ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላትን በሚያይበት ጊዜ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply