You are currently viewing #አዲስ አበባ ወለቴ ፉሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ  የክርስትና እምነት ተከታዩች እና የአማራ ተወላጆች በግፍ ታስረው እንደሚገኙ ተገለፀ! የካቲት 8 ቀን 2…

#አዲስ አበባ ወለቴ ፉሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የክርስትና እምነት ተከታዩች እና የአማራ ተወላጆች በግፍ ታስረው እንደሚገኙ ተገለፀ! የካቲት 8 ቀን 2…

#አዲስ አበባ ወለቴ ፉሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የክርስትና እምነት ተከታዩች እና የአማራ ተወላጆች በግፍ ታስረው እንደሚገኙ ተገለፀ! የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ልዩሃይል በግፍ የታሰሩ የቅድስት ቤተክስስቲያን አማኞች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምመናን በግፍ ታስረው እንደሚገኙ መንጮች ለአሻራ ሚድያ ተናግረዋል። በመዲናዋ አዲስ አበባ ውስጥ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና በደል ተባብሶ ቀጥሏል ያሉት ምንጮቻችን በሽህወች የሚቆጠሩ አማሮች ደግሞ አዋሽ አርባ በኦሮሚያ ልዩሃይል በግፍ ታስረው ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል። በተለይም ከሰሞኑ ካለምንም ምክንያት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩች በመሆናቸው ብቻ በየቀኑ ከመሃል አዲስአበባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች እየታፈኑ ወደአዋሽ አርባ እና የተለያዩ አካባቢዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ምጮች አረጋግጠዋል። አዲስ አበባን ወለጋ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው አገዛዙ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ብለዋል። ከሰሞኑ ህገወጥ ቡድኑ በኦሮሞ የታጠቁ ሃይሎች ታጅቦ ወለቴዩሐንስ ቤተክርትያን ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር በተፈጠረው ግርግር ቤተክርስቲያንን አናስደፍስም በማለት ፊትለፈት ሲጋፈጡ የነበሩ የቅድስት ቤተክርትያን አማኞች በጥይት አለርህራሄ ተደብድበው አንድ ወጣት ህወቱ ያለፈ ሲሆን በርካቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል። በመሆኑም አሁንም ድረስ የክርስትና እምነት ተከታዩች በግፍ እየታፈኑ ይገኛሉ።ይህን ድርጊት ሁላችንም በቃ ልንለው ይገባል ሲሉም ጨምረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply