አዲስ አበባ ውስጥ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ

https://gdb.voanews.com/FA4833D6-2B54-4A3D-A0C4-AD1AEC767811_cx0_cy5_cw0_w800_h450.jpg

በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መካኒሳ፤ የመካነ እየሱስ ሴሚናር ግቢ ነዋሪዎች መካከል የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የመካነ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ በዐስራ ስምንት አባወራ ላይ አደጋው መድረሱን ገልፀዋል። 

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply