አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ7 መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አጸደቀ

ማክሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ባካሄደው ስብሰባ 7 መምህራንን ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አጽድቋል።

የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ከመቅረቡ በፊት በአገር ውስጥና ውጭ ባለሞያዎች ተገምግሞ፣ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት እና በሚያስተምሩበት ትምህርት ክፍል ተቀባይነትን አግኝቶ የተሰጠ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው መምህራን፦

1. ፕ/ር ስዩም ለታ አስፋው (በኢንቫይሮሜንታል ባዮቴክኖሎጂ)፣

2. ፕ/ር ሀሰን ማሞ እድሪስ (በፓራሲቶሎጂ)፣

3. ፕ/ር ፈለቀ ዘውገ በሻህ (በኢንቫይሮሜንታል ኬምስትሪ)፣

4. ፕ/ር ግርማ ስዩም ጌድዮን (በአናቶሚ)፣

5. ፕ/ር ጉርጃ በላይ ወ/ሚካኤል (በሞለኪዩላር ጄኔቲክስ)፣

6. ፕ/ር አሰፋ አበጋዝ ይመር (በመሬት አጠቃቀም አስተዳደር) እና

7. ፕ/ር ተሻለ ሶሪ ቶሌራ (በቬተሪናሪ ኢፒዲሞሎጂ) መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

The post አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ7 መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አጸደቀ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply