አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራና በአፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቶችን እንደሚያጠና አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራና በአፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቶችን እንደሚያጠና አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጥናትና የምርምር ቡድን በማቋቋም በሽብር ቡድኑ አማካኝነት በአማራና በአፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊ ጥሰቶችንና የንብረት ውድመቶችን እንደሚያጠና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። የተለያዩ ተመራቂ ተማሪዎችም የደረሱ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን እንዲያጠኑ ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጿል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ በአገራችን ጦርነት በነበረባቸው የአማራና አፋር ክልሎችና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን የሕይወትና የንብረት ውድመት በመስክ የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የጥናትና የምርምር ስራ ጀምሯል። ከጥናትና ምርምር ቡድኑ የሚገኘው የጥናት ግኝት መሠረት በማድረግም ውድመቱን ያደረሰውን አሸባሪውን ቡድን የታሪክ ተወቃሽ ለማድረግና በቀጣይ ለሚኖሩ ለጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲውል ብለዋል። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸማቸው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶች እጅግ ዘግናኝና የሰው ልጅ በወገኑ ላይ ይፈጽማቸዋል ተብሎ እንደማይታሰብ ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply