አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀንና በማታ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል፡፡

ከተመራቂዎቹ መሀከል 48ቱ በ3ኛ ዲግሪ በቀን ያሰለጠናቸውን ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም 809፣ በቀን 3039 እንዲሁም በርቀት 18 ተማሪዎቹን ለምርቃት አብቅቷል፡፡

በህክምና ስፔሻሊቲም 26 ተማሪዎቹ ዛሬ ከሚመረቁት መሀከል መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ዛሬ ከተመረቁት መሀከል 2635 ወንዶች ሲሆኑ 1452 ሴቶች ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአመቱ በአጠቃላይ 10561 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከእነዚህ መሀከል 5045 በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ 313 በ3ኛ ዲግሪ እና 2226 በማታ ፕሮግራም ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም በርቀት 180፣ በክረምት 2252፣ በስፔሻሊቲ 265፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ በመምህርነት ፕሮግራም 269 ናቸው፡፡

በአመቱ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 7350 ወንዶችን እና 3211 ሴቶች ተማሪዎቹን ለምረቃ አብቅቷል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply