
#አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ፣ ማሪያም ሰፈር ! መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአዲስ አበብ ጀሞ ሚካኤል ፣ ማርያም ሰፈር 14ቱ የማህበር ስላሴ የፅዋ ማህበር አባላት በድጋሜ ታፍነው ታሰሩ። ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጥምቀት በዓልን ሲያከብሩ በነበረበት አፍነው አስረው ለእያንዳንዳቸው በ200 ብር ዋስ የተፈቱ ሲሆን ፣ በድጋሜ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አፍነው አስረዋቸዋል።በአዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ከ14ቱ የፅዋ ማህበር ከታፈኑት አባላት 5ቱ የፅዋ ማህበር አባላት እስካአሁን የት እንዳሉ አይታወቅም።በግፍ ከታፈኑትም መካከል 1/መምህር ደመቀ አቤ 2/ ፖሊስ ሙሉጌታ ሀብቴ 3/አዲሱ ፀሐይ 4/ ገዛህኞ 5/ ተንሳይ እስካሁን ድረስ አፍነው መውሰዳቸውን እንጅ የት እንደደረሱ ማውቅ አልቻልንም። ታፍነው የታሰሩ የስላሴ የፅዋ ማህበር አባላቱ የታሰሩት በማንነታቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ ነው።የፅዋ ማህበር አባላቶች የታሰሩት የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ቢሆንም እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post