
አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ፣ ማሪያም ሰፈር አካባቢ በመንግስት የጸጥታ አካላት የታፈኑ የአማራ ልጆችን አድራሻቸው ለማወቅ አልተቻለም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ፣ ማርያም ሰፈር 14ቱ የማህበር ስላሴ የፅዋ ማህበር አባላት በድጋሜ ታፍነው መታሰራቸው ተገልጧል። ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጥምቀት በዓልን ሲያከብሩ በነበረበት አፍነው አስረው ለእያንዳንዳቸው በ200 ብር ዋስ የተፈቱ ሲሆን ፣ በድጋሜ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አፍነው አስረዋቸዋል። በአዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ከ14ቱ የፅዋ ማህበር ከታፈኑት አባላት 5ቱ የፅዋ ማህበር አባላት እስካአሁን የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል። በግፍ ከታፈኑትም መካከልም:_ 1) መምህር ደመቀ አቤ፣ 2) ፖሊስ ሙሉጌታ ሀብቴ፣ 3) አዲሱ ፀሐይ፣ 4) ገዛህኝ እና 5) ተንሳይ የተባሉ ይጠቀሳሉ። እስካሁን ድረስ ታፍነው መውሰዳቸውን እንጅ የት እንደደረሱ ማወቅ አልቻልንም፤ ታፍነው የታሰሩ የስላሴ የፅዋ ማህበር አባላቱ የታሰሩትም በማንነታቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ መሆኑ ተመላክቷል። ምንጭ_አሻራ ሚዲያ
Source: Link to the Post