You are currently viewing “አድዋን ካለ ንጉሱና ንግስቲቱ መዘከር የታሪክ ክህደት ማሳያ ነው‼” ደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …    የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

“አድዋን ካለ ንጉሱና ንግስቲቱ መዘከር የታሪክ ክህደት ማሳያ ነው‼” ደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

“አድዋን ካለ ንጉሱና ንግስቲቱ መዘከር የታሪክ ክህደት ማሳያ ነው‼” ደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ 127ኛ የዓድዋ ድል በዓል “አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት” በሚል መሪ ቃል በታሪካዊቷ ወረኢሉ ከተማ ይከበራል !! የአድዋ ድል የእምዬ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱ ብሎም የሌሎች ቆራጥ፣ በሳል እና ጥበብ የተሞላበት አመራር ሰጭነት ቁልፍ ሚና የተጫወተ መሆኑ ግልጽ ነው። የአድዋዋ ንግስት እቴጌ ጣይቱ:_ “እኔ ሴት ነኝ። ጦርነት አልወድም ነገር ግን በሀገሬ ከመጡብኝ ግን ምቴን እመርጣለሁ። ለሃገር ህይወትን መስዋዕት ማረግ ምን ያህል የተከበረ ሞት ነው ።” ማለታቸው እና በሀገራቸው የማይደራደሩ ስለመሆናቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል። ይህ የድል በዓል በተለይ ወረኢሉ ላይ በድምቀት ይከበራል። ወረኢሉ ቋንቋችን የተለያዬ የመሰለው ጣሊያን ለሀገር ጉዳይ በአንድ የምንደማመጥ እንደሆንን ያደመጠበት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው፡፡ ንጉስ ሚኒሊክ ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና ያገሬ ሠው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ ብለው አዋጅ ካወጁ በኋላ የአድዋ ድል የጀመረው የቀጠሮው ቦታ ነው፡፡ የቀጠሮው ቦታ የቃል ኪዳን ውል ታተመበት፡፡ ደግሞ ንጉሠ ነገሥቱ አንድም አስቀድመው የሚወዷት የባፈና መሬት፣ የልጃቸው እናት ምድር ብትሆንም ወረኢሉ እንገናኝ ዋናው ምስጢር ግን ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ የወረኢሉ ሰው ጎተራው ሙሉ ነው፡፡ መስኩ ምርት ይሰጣል፡፡ ልቡ ደግ አብልቶ የማይጠግብ ነው፡፡ ጥቅምት እኩሌታ ሀገር ሲከት አንዳች ሳይጎድልበት ሆ ብሎ ወደ አድዋ እንዲዘምት ምክንያት ሆኗል፡፡ ወረኢሉ መርቃ ሸኘች፡፡ ሀገር ወደ ሀገሩ ጠላት ተመመ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው አምባላጌ፣ ከዚያ በኋላ ነው የእንዳ ማርያም ከዚያ በኋላ ነው አድዋ፤ ከዚያ በኋላ ነው የጥቁር ድል፡፡ ወረኢሉ የድል ምዕራፍ መግቢያ ዋና በር፦ ነጋሪት ተጎስሟል፣ የጦር ስትራቴጅ ተነድፎል፣ ጦር መሪወች ተሰይመዋል ፣ አግረኞችና ፈረሰኞች አሰላለፍ ተሠርቶል፣ የአሸናፊነት ስነልቦና ተሰንቆል፣ የስንቅና ትጥቅ ዝግጅት ተካሂዶል፣ የእምነት አባቶች ከነ ታቦታቸውና ቅዱስ ቁርዓናቸው ዘምተዋል፣ ህዝቡ እንግዳ ተቀባይነቱን የሠራዊቱን እግር በማጠብ ማሩ ቅቤውንና እሸቱን እያቀረበ አስተናግዷል፣ የነፃነት ፋይዳ ተሰብኳል፣ ማን በነገረው ለጣሊያን ደርሶ ሚካኤል መጣ ረመጥ ለብሶ ተብሎ የተገጠመላቸው ንጉስ ሚካኤል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር ከወሎ ህዝብ አሰልፈው በሶሶት ግንባሮች ድል አስመዝግበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply