You are currently viewing “አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል።” መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አ…

“አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል።” መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አ…

“አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል።” መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ሀምሌ 5/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በትብብር እየሰሩ የቆዩ ሶስቱ (መኢአድ፣ እናት እና ኢህአፓ) የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ሁለት አቻዎቻቸው (አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ) አብረው በላቀ ትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የገለጹ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀምሌ 5/2015 ስድስት ኪሎ በሚገኘው በእናት ፓርቲ ቢሮ በመገኘት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በእለቱ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተገኙ ጋዜጠኞች ጥያቄዎችን አንስተው በፓርቲ አመራሮች በኩል ምላሽ ተሰጥቷል። የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው:_ አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል። በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ከኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ:_ በአገራችን ኢትዮጵያ ከሶስት አሰርተ ዓመጋት በላይ በተጠና መልኩ እየተተገበረ የሚገኘው የጎሳ ፖለቲካ መራራ ፍሬ አፍርቶ ህዝቧ የመከራ እና የሰቆቃ ህይወት ማሳለፍ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመከራው እና የሰቆቃው መጠን ከእለት እለት ከመሻል ይልቅ ይበልጥ ስር እየሰደደ እና እየከፋ የሄደ ሲሆን አለም በዝምታ እያዬ አንድ ሚሊዮን ህዝብ ካለቀበት ከሩዋንዳው የዘር ፍጅት በኋላ በአፍሪካ መጠነ ሰፊ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ መጋሪ አያሻም። ልክ እንደ ሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ አለም ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ ዓመታት እየሆነ ያለውን ባላዬ እያለፈ ይገኛል። በዚሁ አገር በጀመረችው የጥፋት ጉዞ እና የዚሁ ውጤት በሆነውና የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን የአለማችን ከፍተኛው ደም አፋሳሽ ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎቻችን ህይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በመንግስት መግለጫ መሰረት በትሪሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ንብረት ወድሟል። በሌላ በኩል ባለፉት አምስት ዓመታት ዜጎች በቀያቸው፣ በማንነታቸው ተለይተው በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፤ ቤታቸው ፈርሶ ለስደት እና ተረጅነት ተጋልጠዋል። በእነዚህ ማንነት ተኮር ጥቃቶች ግንባር ቀደም ሰለባ የሆነው የአማራው ማህበረሰብ በቅርቡ በወጣው ዘገባ ከ25 ሽህ እስከ 40 ሽህ የሚደርሱ ዜጎች ለውጥ መጣ በተባለበት ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተዘግቧል። ይህ ሁሉ የዛሬይቷ አገራችን ኢትዮጵያ በዜጎጎቿ እና በአለም ማህበረሰብ ዘንድ የምትታወቅበት ወቅታዊ መገለጫዎች ቢሆንም አገራችን ከቀን ወደ ቀን ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ እያመራች መንግስት በአንዳንድ አካባቢ ምንም እንዳልተፈጠረ በቸልታ በመመልከት በሌላ አካባቢ ቀውሱን ራሱ በመፍጠር እና በማባባስ ለአገር ወደ ከፋ ቀውስ መግባት የማይገባውን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኑሮ ውድነት ህዝባችንን እንዴት እንዳጎበጠው በዚህ መግለጫ መናገር ሳያስፈልግ ነኘበአገራችን በተተገበረው የጎሳ ፌደራላዊ አወቃቀር ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የሚይዙትየኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በሰላም እጦት ቀውስ ውስጥ የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የኦሮሚያ ክልል ከፊል አካባቢ መንግሥት ኦነግ ሸኔ በሚለውና ራሱን የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ስር ወድቆ የኦሮሞ ማህበረሰብ በአንድ በኩል በመንግስት በሌላ በኩል በታጣቂ ኃይሎች ቀንበር ስር ወድቆ አራት ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ የሚገኝ ሲሆን በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪ የአማራ ማህበረሰብ ዜጎቻችን ደግሞ በማንነታቸው ምክንያት ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት እና እየተገደሉ ያሉበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። በዚሁ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰሚ ያጣው ደግሞም ለወራት የቀጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አካባቢውን እየናጠ ይገኛል። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ኢመደበኛ ኃይል ብሎ መንግስት ስያሜ በሰጠው ፋኖ ላይ በከፈተው ጥቃት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የግጭት አውድማ እንዲሆን እየተደረገ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት በየቦታው ኢመደበኛ ኃይሎችን ኢላማ በማድረግ ሽፋን ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር የማያቋርጥ ግጭት ውስጥ ገብቷል። በዚህም ብዙ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። በሚደርሱ የደፈጣ ጥቃቶች በየቦታው የመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት መገደል የእለት ተእለት ክስተት ሆኗል። የአገራችን ነባራዊ እዉነታ ይህ ሆኖ ሳለ የፌደራል መንግስቱም ሆነ የሁለቱም ክልሎች መንግስታት በማያቋርጥ ስብሰባ ተጠምደው ነገሮችን ከማመንዠክ በዘለቀ አገር ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ አምነው በመቀበል አገርን ካንዣበባት ሁለንተናዊ የጥፋት አደጋ ለመታደግ የሚደረግ ሙከራ እንደሌለ የኢትዮጵያ ህዝብም፣ የአለም ማህበረሰብም እየተመለከተ ያለ ጉዳይ ነው። በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም እንደሚባለው አገር እየተከተለች ባለችው ጎዳና የስልጣን ወንበሩን የተቆናጠጠው መንግስትም ስልጣኑን ጨብጦ እንደማይዘልቅ አገርም እንደ አገር አንድነቷን እና ህልውናዋ ተጠብቆ እንደማትቀጥል ይልቁን ሁለት መቶ ዓመታት ወደ ኋላ ተመልሳ በጦር አበጋዞች ልትመራ የምትችልበት እና የዘመነ መሳፍንት አይነት እጣፈንታ ሊያጋጥማት የመቻል እድል እጅግ የሰፋ መሆኑንበቆም ብሎ በሰከነ መንፈስ መረዳት ያሻል። ከዚህ በመነሳት አስቸኳይ የአገር አድን እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ኢትዮጵያዊያን ችግሮቻችን ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረ ተወያይተን መፍታት እንደምንችል ይህን ለማድረግ ጥበቡንም እውቀቱንም ችሎታውም እንዳለን በማመን እኛ በትብብር የምንሰራ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለወቅታዊ የአገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄው ስልጣን ላይ ባለው መንግስት ነፍጥ አንስተው ውጊያ ላይ በሚገኙ ኃይሎች እና ህጋዊ እውቅና ኖሯቸው በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በእኛው ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት የሚመራ፣ ወዳጅ አገራት በደጋፊነት የሚሳተፉበት አስቸኳይ የአገር አድን ውይይት ማድረግ መሆኑን እናምናለን። ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው በሙሉ የአገርን ህልውና የመታደግ እንቅስቃሴን ቸል ባለማለት በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲገባ የአገሩ ጉዳይ እንደሚገደውና የተደራጀ የፖለቲካ ኃይል የጥሪ ደወል እናሰማለን፤ ለተግባራዊነቱም እኔነትን ወደ ጎን ትተን ሁሉም በጋራ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ አገርን የማዳን ውይይቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ስብሰባው ኢትዮጵያዉያን መራሽ ሆኖ በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ የተሻለ ጎዳና ላይ በሚገኝ የአፍሪካ አገር ርዕሰ ከተማ ቢካሄድ ለተሳታፊዎች የደህንነት ስጋትን ለማስወገድ እንደ አፍሪካዊት አገር ለአፍሪካ ችግር መፍትሄውን እኛው አፍሪካውያን በዚሁ ማፈላለግና ማግኘት እንደምንችል በማሳያነት ልንጠቀምበትና በዴሞከራሲ ሥርዓት መልካም ስም ባላት አገር መከናወኑ በአስተማሪነቱ ጠቀሜታ ሊኖረው እንደሚችል መጥቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህ አገርን የመታደግ አስቸኳይ ውይይት መንግስት በአዋጅ ካቋቋመዉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ጋር የማይቀላቀልና ሊምታታ የማይገባው ሲሆን አገር ላይ ላንዣበበዉ የህልዉና አደጋ በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የሚደረግ የህልውና አደጋን ማስወገጃ የአደጋ ጊዜ መውጫ ሥራ ነው፡፡ በአገር አድን ውይይቱ መንግሥት እንደ አንድ ተወያይ አካል የሚቀርብበት ሲሆን በሌላ በኩል ነፍጥ አንስተው የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ታጣቂ የአማራ ኃይሎች እንዲሁም በህጋዊ መልኩ ተመዝግበዉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ሲሆን ይህን በማድረግ አገርን ከከፋዉ ጥፋት መታደግ ይሆናል። በዚህ መሠረት:_ 1) የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ሃሳብ ተቀብሎ እንደ መንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ በአስቸኳይ ቀን ወስኖ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀምር፤ 2) መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት ለማረጋገጥ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በፌዴራል ፖሊስ፣ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች እስር ቤት በጅምላ አጉሮ የሚያሰቃያቸውን የህሊሊናና የማንነት እስረኞች እንዲፈታ፣ 3) የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ታጣቂ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በዚህ አገርን የመታደግ ዓላማ ባነገበ ዉይይት እንዲፈቱ የሚፈልጉዋቸዉን ጥያቄዎቻቸዉን በመለየት የዉይይቱ ተሳታፊዎቻቸዉን ዝግጁ እንዲያደርጉ፤ 4) የአገር ጉዳይ ግድ የሚላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት አገር ከገባችበት ቀዉስ እንድትወጣ አስፈላጊዉን ዝግጅት በማድረግ የመፍትሄ አካል በመሆን አገርን ከጥፋት የሚታደግ ሃሳብ በማመንጨትና በማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጡ፣ 5) የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ መስራች አባል እንደሆነችበትና መቀመጫዉን እንዳደረገባት አገር በአገራችን እያንዣበበ ያለው አደጋ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና፣ በምሥራቅ አፍሪካና በአጠቃላይ አህጉሩ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን እጅግ አደገኛ የሆነ ተጽዕኖ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ውይይቱ በአህጉራዊው ተቋም የቅርብ እይታ በእህት የአፍሪካ አገር መዲና ሊከናወን የሚችልበትን እንዲያመቻች፣ 6) የወዳጅ አገራት መንግሥታት ኢትዮጵያ ካላት ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችል የህልውና አደጋ በአካባቢ አገራትና በአፍሪካ ቀንድ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በአግባቡ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህን ኢትዮጵያውያን የአገራችንን ህልውና ለመታደግ የምናደርገውን ጥረት አስፈላጊ የሆነዉን የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍና እገዛ በማድረግ እንዲደግፉ፤ 7) የእምነት ተቋማት የታለመዉ ዓላማ ተሳክቶ አገር ከጥፋትና ሁለንተናዋ ቀዉስ እንድትድን በጸሎት ተግታችሁ እንድታስቡ፤ 8) በመጨረሻም ከሁሉ በላይ የችግሩና የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ሆነህ ለግማሽ ምዕተ ዓመት የኖርከውና ዛሬም የመከራ ቀንበር ተሸከመህ በሥጋት የዕለት ተለት ኑሮህን እንድትመራ የተገደድከው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ ዘመንህ እንዲያበቃ በምትችለው መንገድ ኹሉ አገርህን ከጥፋት ጎዳናና ከመፍረስ ለመታደግ ተግተህ እንድትሠራ በአገርህ ላይ ያንዣበበው የህልውና አደጋ ተወግዶ በሰላም ወጥተህ መግባት እንድትችል በምናደርገው ጥረት ከጎናችን እንድትቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ከላይ የተጠቀሰዉ አገርን የማዳን ፈጣን ተግባር በዋነኛነት መንግሥት ሊተገብረዉ እንደሚገባ በማመን በአስቸኳይ ወደ ተግባር እንዲተረጉመዉና አገራችንን ከሁለንተናዊ ቀዉስና ጥፋት እንዲታደግ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ መንግሥት ይህን ማድረግ ካልቻለ ወይንም ፈቃደኛ ካልሆነ ትናንት የነበሩ መሪዎች ዛሬ እንደሌሉ ሁሉ ዛሬ የሥልጣን ወንበር የተቆናጠጡ መሪዎችም ለዘላለም እንደማይዘልቁና አገርና ሕዝብ የሁሉም መሠረትና ምንጭ መሆናቸውን በጽኑ በማመን የስልጣን ወንበር ባንይዝም የአገር አንድነትን የማጽናት ኃላፊነት ያለብን መሆኑን በማመን ለዚህ ሁሉን አቀፍ አገርን ከህልውና አደጋ የመታደግ ዉይይት መሳካት አቅማችን በፈቀደ ወደፊት እንደምንራመድና እዉን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደምንሠራ እናሳስባለን፡፡ መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ “አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል።” መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሀምሌ 5/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በትብብር እየሰሩ የቆዩ ሶስቱ (መኢአድ፣ እናት እና ኢህአፓ) የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ሁለት አቻዎቻቸው (አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ) አብረው በላቀ ትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የገለጹ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀምሌ 5/2015 ስድስት ኪሎ በሚገኘው በእናት ፓርቲ ቢሮ በመገኘት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በእለቱ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተገኙ ጋዜጠኞች ጥያቄዎችን አንስተው በፓርቲ አመራሮች በኩል ምላሽ ተሰጥቷል። የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው:_ አገራችን ኢትዮጵያ ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሰፈልጋል። በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ከኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ:_ በአገራችን ኢትዮጵያ ከሶስት አሰርተ ዓመጋት በላይ በተጠና መልኩ እየተተገበረ የሚገኘው የጎሳ ፖለቲካ መራራ ፍሬ አፍርቶ ህዝቧ የመከራ እና የሰቆቃ ህይወት ማሳለፍ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመከራው እና የሰቆቃው መጠን ከእለት እለት ከመሻል ይልቅ ይበልጥ ስር እየሰደደ እና እየከፋ የሄደ ሲሆን አለም በዝምታ እያዬ አንድ ሚሊዮን ህዝብ ካለቀበት ከሩዋንዳው የዘር ፍጅት በኋላ በአፍሪካ መጠነ ሰፊ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ መጋሪ አያሻም። ልክ እንደ ሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ አለም ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ ዓመታት እየሆነ ያለውን ባላዬ እያለፈ ይገኛል። በዚሁ አገር በጀመረችው የጥፋት ጉዞ እና የዚሁ ውጤት በሆነውና የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን የአለማችን ከፍተኛው ደም አፋሳሽ ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎቻችን ህይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በመንግስት መግለጫ መሰረት በትሪሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ንብረት ወድሟል። በሌላ በኩል ባለፉት አምስት ዓመታት ዜጎች በቀያቸው፣ በማንነታቸው ተለይተው በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፤ ቤታቸው ፈርሶ ለስደት እና ተረጅነት ተጋልጠዋል። በእነዚህ ማንነት ተኮር ጥቃቶች ግንባር ቀደም ሰለባ የሆነው የአማራው ማህበረሰብ በቅርቡ በወጣው ዘገባ ከ25 ሽህ እስከ 40 ሽህ የሚደርሱ ዜጎች ለውጥ መጣ በተባለበት ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተዘግቧል። ይህ ሁሉ የዛሬይቷ አገራችን ኢትዮጵያ በዜጎጎቿ እና በአለም ማህበረሰብ ዘንድ የምትታወቅበት ወቅታዊ መገለጫዎች ቢሆንም አገራችን ከቀን ወደ ቀን ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ እያመራች መንግስት በአንዳንድ አካባቢ ምንም እንዳልተፈጠረ በቸልታ በመመልከት በሌላ አካባቢ ቀውሱን ራሱ በመፍጠር እና በማባባስ ለአገር ወደ ከፋ ቀውስ መግባት የማይገባውን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኑሮ ውድነት ህዝባችንን እንዴት እንዳጎበጠው በዚህ መግለጫ መናገር ሳያስፈልግ ነኘበአገራችን በተተገበረው የጎሳ ፌደራላዊ አወቃቀር ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የሚይዙትየኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በሰላም እጦት ቀውስ ውስጥ የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የኦሮሚያ ክልል ከፊል አካባቢ መንግሥት ኦነግ ሸኔ በሚለውና ራሱን የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ስር ወድቆ የኦሮሞ ማህበረሰብ በአንድ በኩል በመንግስት በሌላ በኩል በታጣቂ ኃይሎች ቀንበር ስር ወድቆ አራት ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ የሚገኝ ሲሆን በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪ የአማራ ማህበረሰብ ዜጎቻችን ደግሞ በማንነታቸው ምክንያት ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት እና እየተገደሉ ያሉበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። በዚሁ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰሚ ያጣው ደግሞም ለወራት የቀጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አካባቢውን እየናጠ ይገኛል። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ኢመደበኛ ኃይል ብሎ መንግስት ስያሜ በሰጠው ፋኖ ላይ በከፈተው ጥቃት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የግጭት አውድማ እንዲሆን እየተደረገ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት በየቦታው ኢመደበኛ ኃይሎችን ኢላማ በማድረግ ሽፋን ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር የማያቋርጥ ግጭት ውስጥ ገብቷል። በዚህም ብዙ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። በሚደርሱ የደፈጣ ጥቃቶች በየቦታው የመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት መገደል የእለት ተእለት ክስተት ሆኗል። የአገራችን ነባራዊ እዉነታ ይህ ሆኖ ሳለ የፌደራል መንግስቱም ሆነ የሁለቱም ክልሎች መንግስታት በማያቋርጥ ስብሰባ ተጠምደው ነገሮችን ከማመንዠክ በዘለቀ አገር ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ አምነው በመቀበል አገርን ካንዣበባት ሁለንተናዊ የጥፋት አደጋ ለመታደግ የሚደረግ ሙከራ እንደሌለ የኢትዮጵያ ህዝብም፣ የአለም ማህበረሰብም እየተመለከተ ያለ ጉዳይ ነው። በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም እንደሚባለው አገር እየተከተለች ባለችው ጎዳና የስልጣን ወንበሩን የተቆናጠጠው መንግስትም ስልጣኑን ጨብጦ እንደማይዘልቅ አገርም እንደ አገር አንድነቷን እና ህልውናዋ ተጠብቆ እንደማትቀጥል ይልቁን ሁለት መቶ ዓመታት ወደ ኋላ ተመልሳ በጦር አበጋዞች ልትመራ የምትችልበት እና የዘመነ መሳፍንት አይነት እጣፈንታ ሊያጋጥማት የመቻል እድል እጅግ የሰፋ መሆኑንበቆም ብሎ በሰከነ መንፈስ መረዳት ያሻል። ከዚህ በመነሳት አስቸኳይ የአገር አድን እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ኢትዮጵያዊያን ችግሮቻችን ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረ ተወያይተን መፍታት እንደምንችል ይህን ለማድረግ ጥበቡንም እውቀቱንም ችሎታውም እንዳለን በማመን እኛ በትብብር የምንሰራ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለወቅታዊ የአገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄው ስልጣን ላይ ባለው መንግስት ነፍጥ አንስተው ውጊያ ላይ በሚገኙ ኃይሎች እና ህጋዊ እውቅና ኖሯቸው በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በእኛው ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት የሚመራ፣ ወዳጅ አገራት በደጋፊነት የሚሳተፉበት አስቸኳይ የአገር አድን ውይይት ማድረግ መሆኑን እናምናለን። ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው በሙሉ የአገርን ህልውና የመታደግ እንቅስቃሴን ቸል ባለማለት በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲገባ የአገሩ ጉዳይ እንደሚገደውና የተደራጀ የፖለቲካ ኃይል የጥሪ ደወል እናሰማለን፤ ለተግባራዊነቱም እኔነትን ወደ ጎን ትተን ሁሉም በጋራ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ አገርን የማዳን ውይይቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ስብሰባው ኢትዮጵያዉያን መራሽ ሆኖ በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ የተሻለ ጎዳና ላይ በሚገኝ የአፍሪካ አገር ርዕሰ ከተማ ቢካሄድ ለተሳታፊዎች የደህንነት ስጋትን ለማስወገድ እንደ አፍሪካዊት አገር ለአፍሪካ ችግር መፍትሄውን እኛው አፍሪካውያን በዚሁ ማፈላለግና ማግኘት እንደምንችል በማሳያነት ልንጠቀምበትና በዴሞከራሲ ሥርዓት መልካም ስም ባላት አገር መከናወኑ በአስተማሪነቱ ጠቀሜታ ሊኖረው እንደሚችል መጥቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህ አገርን የመታደግ አስቸኳይ ውይይት መንግስት በአዋጅ ካቋቋመዉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ጋር የማይቀላቀልና ሊምታታ የማይገባው ሲሆን አገር ላይ ላንዣበበዉ የህልዉና አደጋ በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የሚደረግ የህልውና አደጋን ማስወገጃ የአደጋ ጊዜ መውጫ ሥራ ነው፡፡ በአገር አድን ውይይቱ መንግሥት እንደ አንድ ተወያይ አካል የሚቀርብበት ሲሆን በሌላ በኩል ነፍጥ አንስተው የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ታጣቂ የአማራ ኃይሎች እንዲሁም በህጋዊ መልኩ ተመዝግበዉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ሲሆን ይህን በማድረግ አገርን ከከፋዉ ጥፋት መታደግ ይሆናል። በዚህ መሠረት:_ 1) የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ሃሳብ ተቀብሎ እንደ መንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ በአስቸኳይ ቀን ወስኖ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀምር፤ 2) መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት ለማረጋገጥ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በፌዴራል ፖሊስ፣ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች እስር ቤት በጅምላ አጉሮ የሚያሰቃያቸውን የህሊሊናና የማንነት እስረኞች እንዲፈታ፣ 3) የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ታጣቂ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በዚህ አገርን የመታደግ ዓላማ ባነገበ ዉይይት እንዲፈቱ የሚፈልጉዋቸዉን ጥያቄዎቻቸዉን በመለየት የዉይይቱ ተሳታፊዎቻቸዉን ዝግጁ እንዲያደርጉ፤ 4) የአገር ጉዳይ ግድ የሚላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት አገር ከገባችበት ቀዉስ እንድትወጣ አስፈላጊዉን ዝግጅት በማድረግ የመፍትሄ አካል በመሆን አገርን ከጥፋት የሚታደግ ሃሳብ በማመንጨትና በማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጡ፣ 5) የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ መስራች አባል እንደሆነችበትና መቀመጫዉን እንዳደረገባት አገር በአገራችን እያንዣበበ ያለው አደጋ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና፣ በምሥራቅ አፍሪካና በአጠቃላይ አህጉሩ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን እጅግ አደገኛ የሆነ ተጽዕኖ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ውይይቱ በአህጉራዊው ተቋም የቅርብ እይታ በእህት የአፍሪካ አገር መዲና ሊከናወን የሚችልበትን እንዲያመቻች፣ 6) የወዳጅ አገራት መንግሥታት ኢትዮጵያ ካላት ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችል የህልውና አደጋ በአካባቢ አገራትና በአፍሪካ ቀንድ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በአግባቡ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህን ኢትዮጵያውያን የአገራችንን ህልውና ለመታደግ የምናደርገውን ጥረት አስፈላጊ የሆነዉን የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍና እገዛ በማድረግ እንዲደግፉ፤ 7) የእምነት ተቋማት የታለመዉ ዓላማ ተሳክቶ አገር ከጥፋትና ሁለንተናዋ ቀዉስ እንድትድን በጸሎት ተግታችሁ እንድታስቡ፤ 8) በመጨረሻም ከሁሉ በላይ የችግሩና የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ሆነህ ለግማሽ ምዕተ ዓመት የኖርከውና ዛሬም የመከራ ቀንበር ተሸከመህ በሥጋት የዕለት ተለት ኑሮህን እንድትመራ የተገደድከው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ ዘመንህ እንዲያበቃ በምትችለው መንገድ ኹሉ አገርህን ከጥፋት ጎዳናና ከመፍረስ ለመታደግ ተግተህ እንድትሠራ በአገርህ ላይ ያንዣበበው የህልውና አደጋ ተወግዶ በሰላም ወጥተህ መግባት እንድትችል በምናደርገው ጥረት ከጎናችን እንድትቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ከላይ የተጠቀሰዉ አገርን የማዳን ፈጣን ተግባር በዋነኛነት መንግሥት ሊተገብረዉ እንደሚገባ በማመን በአስቸኳይ ወደ ተግባር እንዲተረጉመዉና አገራችንን ከሁለንተናዊ ቀዉስና ጥፋት እንዲታደግ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ መንግሥት ይህን ማድረግ ካልቻለ ወይንም ፈቃደኛ ካልሆነ ትናንት የነበሩ መሪዎች ዛሬ እንደሌሉ ሁሉ ዛሬ የሥልጣን ወንበር የተቆናጠጡ መሪዎችም ለዘላለም እንደማይዘልቁና አገርና ሕዝብ የሁሉም መሠረትና ምንጭ መሆናቸውን በጽኑ በማመን የስልጣን ወንበር ባንይዝም የአገር አንድነትን የማጽናት ኃላፊነት ያለብን መሆኑን በማመን ለዚህ ሁሉን አቀፍ አገርን ከህልውና አደጋ የመታደግ ዉይይት መሳካት አቅማችን በፈቀደ ወደፊት እንደምንራመድና እዉን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደምንሠራ እናሳስባለን፡፡ መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ

Source: Link to the Post

Leave a Reply