You are currently viewing “አገር ከበቂ በላይ ችግር ስለተሸከመች የተጨማሪ ግጭት ጠመቃ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም‼”        እናት ፓርቲ         አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም_አ…

“አገር ከበቂ በላይ ችግር ስለተሸከመች የተጨማሪ ግጭት ጠመቃ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም‼” እናት ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም_አ…

“አገር ከበቂ በላይ ችግር ስለተሸከመች የተጨማሪ ግጭት ጠመቃ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም‼” እናት ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ:_ መንግሥት ችግሮችን በውይይት ብቻ እንዲፈታ በተደጋጋሚ አጥብቀን እየጠየቅን ባለንበት በዚህ ሰዓት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የግጭት ጠመቃ እንቅስቃሴዎች ተበራክተዋል። በጋምቤላ ክልል በአኝዋክ እና ኑዌር ጎሳዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ደም አፋሳሽ ሆኖ በመቀጠሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዚሁ ክልል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችም ድንበር አልፈው በሕዝባችን ላይ ጥቃት እየፈጸሙና የዜጎቻችንን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ። አገር ጥቃት እየደረሰባት እየተወሰደ ያለ ተግባራዊ የሆነ አጸፋዊ እርምጃ ስለመኖሩ ምንም አይነት ፍንጭ አለመታየቱና መንግሥት ዝምታን መምረጡ ከፍተኛ ጥያቄ ያጭራል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ከሱዳን ተነስቶ ከነትጥቁ ከተማ ገብቶ እንዲሰፍር የተደረገውና ባለፉት ቀናት ከሃያ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው “ታጣቂ ኃይል” በሰላማዊ የማህበረሰቡ ነዋሪዎች ላይ ትልቅ ስጋትን ደቅኗል። በተለይ መንግሥት “ልዩ ኃይል አያስፈልግም” ብሎ ለመበተን እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ባለበት ሁኔታ “ታጣቂ ኃይሉ”ን ከነ ሙሉ ትጥቁ እንዲቀመጥ ማድረጉ የኦነግ ጦር ከኤርትራ በረሀ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የተደረገውን አቀባበልና ያን ተከትሎ አገር እያለፈች ያለችበትን መንገድ መለስ ብለን እንድናስታውስ ያስገድደናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቶዎች የሚቆጠረው ይኸው ታጣቂ ኃይል ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ከሰፈረበት ካምፕ ከነትጥቁ ወጥቶ ጠፋ መባሉ በአካባቢው እየሆነ ካለው ነገር ጀርባ ሊኖር የሚችለውን ሴራ በግልጽ ያመላክታል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው ከጥቂት ቀናት ወዲህ መልሶ እንዲሰፍር የተደረገው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል። “ልዩ ኃይሎች ፈርሰዋል” በተባለበት ሁኔታ በዩኒፎርም እና ሙሉ ትጥቅ ድንገት በአካባቢው መጥቶ መስፈሩ መፍረሱን ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱ በተጨማሪ የአካባቢውን ነዋሪ እንዳይረጋጋ በማድረግ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል። “ለምን!?” የሚል ጥያቄም ያስነሳል። ስለሆነም:_ ፩. በአኝዋክ እና ንዌር ጎሳዎች መካከል በጋምቤላ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት በማስቆም የአገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉ አግባብነት ያለው ሲሆን ቀጣይ በዜጎቻችን መካከል ደም አፋሳሽ ሁኔታ እንዳይከሰት ተጠያቂነት በተላበሰ መልኩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እናሳስባለን። ፪. መንግሥት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከነሙሉ ትጥቁ በካምፕ እንዲቀመጥ ያደረገውና አሁን ላይ መጥፋቱ የተነገረው ታጣቂ ኃይል በአሁኑ ሰዓት በነዋሪዎች ላይ ትልቅ የአደጋ ስጋት የደቀነ መሆኑ ታውቆ መከላከያ ሠራዊት አስፈላጊውን የዜጎች ደኅንነት የመጠበቅ ሥራ በመሥራት የሰፈነውን ሥጋት እንዲያስወግድ እንጠይቃለን። ፫. በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው ላይ መልሶ እንዲሰፍር የተደረገው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ለምን መስፈር እንዳስፈለገው በግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥበትና ቢያንስ ከዚያ ተነስቶ ለነዋሪው ስጋት የማይሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር እናሳስባለን። በመጨረሻም በእነዚህ ተከታታይ ጥቃቶችና ግጭቶች ህይወታችውን ላጡ ዜጎቻችን እረፍተ ነፈስን ለቤተሰቦቻቸውና ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply