አጫጭር መረጃዎች ስለ ” ዓድዋ ድል መታሰቢያ ”  ፦- በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ  5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። – 8ቱ በሮች ፦* የምሥራቅ…

አጫጭር መረጃዎች ስለ ” ዓድዋ ድል መታሰቢያ ”  ፦

– በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ  5 ወለል እና 8 በሮች አሉት።

– 8ቱ በሮች ፦
* የምሥራቅ ጀግኖች በር፣
* የምዕራብ ጀግኖች በር፣
* የሰሜን ጀግኖች በር፣
* የደቡብ ጀግኖች በር፣
* የፈረሰኞች በር፣
* የአርበኞች በር፣
* የፓንአፍሪካኒዝም በር ተብለው ተሰይመዋል።

– በመታሰቢያው ነጋሪትን ጨምሮ የኢትዮጵያውያን የተለያዩ (ባህላዊዎችን ጨምሮ) የጦር መሳሪያዎች ተቀምጠዋል።

– በዓድዋ ድል መታሰቢያው የአፄ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ሀውልት፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ፈረሶች መታሰቢያ የአርት ሥራዎችም ሰፍረዋል።

– አንድ መቶ ሃያ ሺህ ጀግኖችን የሚዘክር  ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓንአፍሪካኒዝም ንቅናቄ ማሳያነቱንም ይዟል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፋውንቴንም ተሰርቶለታል።

– በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 500 ሰዎችን መያዝ የሚችል የፓንአፍሪካኒዝም አዳራሽ አለው።

– በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 300 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዘመናዊ ሁለገብ አዳራሽ አለው።

– አራት ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል የቤት ውስጥ የስፖርት ሜዳ እና አዳራሽ አለው።

– የህፃናት መጫወቻ፣ የንግድ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎችና የአርት ጋላሪ አለው።

– ከአንድ ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ አለው።

– እያንዳንዳቸው 280 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ 2 ሲኒማ ቤቶች አሉት።

– በቅርቡ ወደ ሀገር የገባችው ” ፀሀይ አውሮፕላን ” በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንድትቀመጥ ተደርጓል።

– አጠቃላይ ስራው 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ℹ️ 00 ኪ.ሜ መነሻ ቦታ ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መሐከል ላይ የሚገኘው የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply