አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና የፊት ማስክ የማድረግ ግዴታ ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ሀገሪቱ የኮሮ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/OtP8IJPuwSwL8noEya3iEN3qhtPn0oEyJnHKKn5SAXnwhMjYV26_mQ-YRgwJcJrot3C0zaZVLF514KbzMvZjRtYaVVyYOAYJyXnlwAky2BOXo8Et3euy37g2CVVe88-w5dKUd4TBHtDG31uXOFhMLmFyrJeYDq6dQxMQ6HfDveor33ECKw1DkxUbjWwHVtSSL4CuKO9fvaO6J5fvv1OXOrMNNXlOps84Ey7cRGorh2snZl8pnkdEYJhHMruSQ5KiW9OSYCPUSXuNeBKLHT5kJGDExb87JLvXGTNJ4xoWxKri7eHM9hcZxDjq9l1suVWiSRMppv6zDj2BAxgNinqkOg.jpg

አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና የፊት ማስክ የማድረግ ግዴታ ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡

በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና የፊት ማስክ የማድረግ ግዴታ ማንሳቷን በዛሬው እለት አስታውቃለች፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሀጄ ጊንጎብ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ማስክ ማድረግን ጨምሮ ኔጌቲቭ የሆኑትም ዜጎች ቢሆኑ ምርመራ ማድረግ ግዴታቸው አይደልም ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ በየሳምንቱ ከ30ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ይያዙ የነበረ ሲሆን አሁን ባለው መረጃ መሰረት በሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከ 222 አይበልጥም ተብሏል፡፡

በናሚቢያ በአማካኝ 14 ያህል ዜጎች የኮሮና ቫይረስ በየቀኑ ቢገኝባቸውም መመርያው መነሳቱን አልጀዚራ ነው የዘገበው፡፡

ከሌላ ሀገር የሚገቡ ዜጎች ሙሉ በሙሉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከወሰዱ ማስክ ማድረግ ግዴታቸው አይደልም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ናሚቢያ እስካሁን ድረስ 1.7 ሚሊዮን ዜጎቿን መከተቧን ዘገባ ጨምሮ አስታውሷል፡፡

ሔኖክ ወገብርኤል
መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply