አፍሪካ የአየር ፀባይ ለውጥን ለመቋቋም 2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ።

ይሁንና አፍሪካ ከዚህ ውስጥ ያላት እጅግ አነስተኛ ገንዘብ ሲሆን እርሱም በእርዳታ የተገኘ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በተለይም በምጣኔ ሃብታቸው ያላደጉ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በእጅጉ እየተቸገሩ እንደሚገኙና ቀውስ ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ይህ ተገለጸው “የአየር ንብረት ደጋፊ ፋይናንስ እና የአለም አቀፍ ተሞክሮዎች” በሚል ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ባሰናዳው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ላይ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ በቀረበው ጥናት መሰረት አሁን ባለው ሁኔታ አፍሪካ የአየር ፀባይ ለውጥን ለመቋቋም 2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋታል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያም ከሚያስፈልጋት 25 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ያገኘችው ግን 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዓለማችን እየጨመረ ባለው የሙቀት መጠን ምክንያት አንዳንድ ስፍራዎች ወደ በረሃነት እየተቀየሩ መሆኑንና በአንጻሩ አንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ደግሞ በከፍተኛ ጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋ እያጋጠማቸው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓየር ጸባይ ለውጥን ተከትሎ በሚደርሱ አደጋዎች በየአመቱ 315 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply