“አፍራሽ በሆነው የህወሀት ሀይል ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ በወቅቱ ባለመውሰዱ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት እውነተኛ የታሪክ ጠላቶቻችን ተላላኪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል”   ነፀ…

“አፍራሽ በሆነው የህወሀት ሀይል ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ በወቅቱ ባለመውሰዱ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት እውነተኛ የታሪክ ጠላቶቻችን ተላላኪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል” ነፀ…

“አፍራሽ በሆነው የህወሀት ሀይል ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ በወቅቱ ባለመውሰዱ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት እውነተኛ የታሪክ ጠላቶቻችን ተላላኪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል” ነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነዐድ) አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነዐድ) ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ትህነግ/ህወሀት በመከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተውን ጦርነት ነውረኛ ሲል አውግዟል። ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፀንታ በኖረችባቸው ለረዥም የነጻነት ዘመናት በተለያዩ ከውስጥም ከውጭም በተነሱ ታሪካዊ ጠላቶቻችን አማካኝነት በተለያዩ ጊዜያት በወራረዎች የተፈተነች ቢሆንም በዜጎቿ የጋራ መስዋዕትነት ሉአላዊነቷን አስከብራ አሁን ላይ መድረሷን ነዐድ አውስቷል። የታሪካዊ ጠላቶቻችን ፍላጎትና አላማ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ከታሪክና ከአለም ካርታ ላይ ለመደምሰስና ከእነ ጭራሹም ለማጥፋት በመሆኑ እቅዳቸውም ጥልቅና ዘመን ተሻጋሪ ነው ያለው ነፀብራቀ አማራ ድርጅት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን በጦር ከመውረር ይልቅ ለጦርነት የሚያውሉትን በጀት በመበጀት በልዩ ልዩ መንስኤዎች እርስ በርሳችን በማባላትና በማጋጨት መንገድ የሚመራ በተጠና እና በተራቀቀ ዘዴ በተለያዩ ገጽታዎች እየተተገበረ በስፋት ቀጥሎ ይገኛል ሲልም አክሏል። እኛም ታሪካዊ ጠላቶቻችን ቀምመውና አቀናብረው ያዘጋጁልንን በማር የተለወሰ መርዝ እየተጎነጨን ትኩረትና አላማችንን ካወቅን በኋላ እንደ ሀገር፣ህዝብና መንግስት ማርከሻ/መፍትሄ ማብጀት ያለመቻላችንን አሳዛኝ እውነታንም ጠቅሷል። ነዐድ እንዳለው ታሪካዊ ጠላቶቻችን በጠረጉልን የጥፋት ጎዳና እየነጎድን፣በቀየሱልን ቦይም እየፈሰስን የራሳችን ሀገር በራሳችን እጅ በማፍረስ ላይ እንገኛለን። ይህን እኩይ የጠላቶቻችንን ሴራ ጠንቅቆ በማወቅ ግንባሩን ሳያጥፍ በሰከነና በበሰለ ሀገርና ህዝብን ማዕከል ባደረገና ከሆያ ሆዬ በፀዳ መልኩ አቋሙን በተለያየ መልኩ ለተለያዩ አካላት ችግሮችን ከእነ መፍትሄያቸው ሲያቀርብ መቆየቱን ነው ነዐድ የጠቀሰው። በተጨማሪም በሀገራችን እየተካሄደ ያለው እልቂት የፖለቲካ አጀንዳ ተይዞለት በህግ የተደገፈ መሆኑን በመግለፅ አበክረን ታግለናል፣ለወደፊትም እንታገላለን ብሏል፤ ነዐድ በመግለጫው። ነዐድ ሲቀጥል የጠላቶቻችን ስትራቴጅ ኢትዮጵያን ማፍረስ ሲሆን እዚህ ለመድረስም በሀይማኖትና በማንነት ላይ የተመሰረተ ዘር ተኮር ፍጅትን ታክቲኮቻቸው አድርገው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል ነው ያለው። እንደ ድርጅቱ እምነት በአማራ ላይ የተደፋው ጥላሸት ሲፀዳ ኢትዮጵያዊነቱ ጎልቶ ስለሚወጣ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት፣ በአጥንቱና የህይወትን መስዋዕትነት የከፈለላት ሀገር እንዳትፈርስ ራሱን አደራጅቶ በመመከት በሀገሩ በእኩልነትና በፍትህ እንዲኖር ትዕግስት እየተላበሰ ራሱን የሚከላከልበትና የሚመክትበትን የትግል ስልት ቀርጾ ሰፊ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል። ይሁን እንጅ ውጤት ያጣነው ከተስፋችን ስጋታችን ማመዘኑ ብቻ ሳይሆን አማራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ዋጋ ከፍሎ ባፀናው ነጻነትና ሀገሩ በየጊዜው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ መካሄዱና መቀጠሉ፣ድርጊቱም በታሪካዊ ጠላቶቻችን ብቻ ሳይሆን በአደረጃጀት የታገዘ የመንግስት ሙሉ ድጋፍ ያለበት እንደሆነ ይሰማናል ብሏል። ነዐድ በጉራፈርዳ፣በበደኖ፣ በአሰቦት፣በሶማሌ ክልል፣በወለጋ፣ በሻሸመኔ፣በመተከልና በወለጋ ጉሊሶ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ያነጣጠረው በአማራ ላይ ቢሆንም ነገር ግን ሞቱ የአማራ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጨረሻው መጀመሪያ መሆኑን በማመን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘውና ቀጥሎም ሊታገለው ይገባል ሲል አሳስቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የጠላታችን አጀንዳ አስፈጻሚ ከመሆን እስከ አሁን ለቀጠለው እልቂት ግንባር ቀደም ተጠያቂው ትህነግ እንደሆነ የጠቀሰው ነዐድ በዚህ አፍራሽ ሀይል ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ በወቅቱ ባለመውሰዱ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት እውነተኛ የታሪክ ጠላቶቻችን ተላላኪነቱን አጠናክሮ ስለመቀጠሉ ገልጧል። ውጤቱ ምንም ይሁን ምን አልፈርስ ያላቸውን ሀገር በህዝቦች እልቂት እንድትደክም፣ ለጠላቶቻችንም ምቹ ሁኔታ የማመቻቸት የትህነግ አካሄድ ነውረኝነቱ በቃላት ብቻ የሚገለፅ አይሆንም ሲል ገልጾታል። ምንም እንኳ በወያኔ የተከፈተው ጦርነት የእርስ በርስ ቢመስልም ትህነግ/ህወሀት የለየለየት ጠላት፣ከጠላትም የከፋ ጠላት በመሆኑም ኢትዮጵያ ሀገሬን እወዳለሁ ብኖርም እንኳ አስተዳደርና ሀገር የየቅል በመሆናቸው ባለን አቅም ከአካባቢያችን ጥበቃ እስከ ጦር ግንባሩ የበኩላችን እገዛ በማድረግ የመከላከያ ሀይሉን በመደገፍ ከመንግስት ጎን እንድንቆም ሲል ነው ነዐድ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ ያቀረበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply