አፍሮ እስያ አለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ “ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን” በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል ።ኤፍ ዚ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የ…

አፍሮ እስያ አለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ “ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን” በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል ።

ኤፍ ዚ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰ የግል ማህበር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር አፍሮ እስያ አለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እያካሄደ ይገኛል ።

ይህ አለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከ ግንቦት 9ቀን እስከ ግንቦት 11/2016ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሏል ።

የአፍሮ እስያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዝከረ ሄኖክ በመግለጫው ላይ ኤክስፖው”ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን” በሚል መሪቃል ነው የተዘጋጀው ብለዋል።

በዚህም ታላቅ ኤክስፖ ላይ ከ4 መቶ በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የጤና ተቋማት እንደሚሳተፉ ተነግረዋል ።

ስራ አስኪያጁ  አቶ ዝክረ ሄኖክ ይህ ኤክስፖ ንግድ ተኮር ሳይሆን ማህበረሰብ ተኮር መሆኑ  ከሌሎች ኤክስፖዎች ለየት ያደርጉታል ብለዋል ።

በመሆኑ በጎ ፍቃደኞችን በመያዝ መንግስታዊ ከሆኑት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ምግብና መዳኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና ሌሎች የግሉን ተቋማት በማካተት  ለማህበረሰቡ ተደራሽ በሚኮንበት መልኩ ነው የተዘጋጀው ብለውናል ።

የአዲስአበባ ምግብና መዳኒት ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ አቶ አሰፋ ተሬሳ በበኩላቸው  በዚህ ኤክስፖ ዜጎች ከሚያገኙት ልዩ ልዩ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ባሻገር በከተማችን ከአስራአንዱም ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ 30 ሺህ የደሀ-ደሃ አቅመ ደካሞች ነፃ የጤና ምርመራና መዳኒት ይሰጣል ብለውናል።

በዚህም ማህበረሰቡ እየመጣ ሊጎበኘውና ሊጠቀምበ ይገባል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ ይህ ኤክስፖ የሚለየው ትብብርን ለማጎልበት ፣ፈጠራን ለማሳየትና በጤናው ኢንዱስትሪ ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ አውንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል ።

በልዑል ወልዴ

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply