#አፍቅሮተ ራስ ወይም ናርሲሲዝም የባህሪ እክል ጉዳቶችናርሲሲዝም ወይም አፍቅሮተ ራስ በመላ አለማችን በብዙዎች ላይ የሚስተዋል የባህሪ እክል መሆኑ ይነገራል፡፡ ይህን የባህሪ እክል የከፋ…

#አፍቅሮተ ራስ ወይም ናርሲሲዝም የባህሪ እክል ጉዳቶች

ናርሲሲዝም ወይም አፍቅሮተ ራስ በመላ አለማችን በብዙዎች ላይ የሚስተዋል የባህሪ እክል መሆኑ ይነገራል፡፡ ይህን የባህሪ እክል የከፋ የሚያደርገው ችግሩ ያለባቸው ሰዎች ትክክል እንደሆኑ ስለሚሰማቸው ህክምና ለማግኘት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡

ለራስ ከፍተኛ ግምት መስጠት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በስፋት እንደሚስተዋል የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ይህ ራስን ከልክ ባለፈ መልኩ የመውደድ የባህሪ እክል ካለበት ሰው ጋር ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉ ሰዎች ችግር ውስጥ መሆናቸውም ይገራል፡፡

በሀገራችን ስለ ናርሲሲዝም ግንዛቤአለ ለማለት ባያስችልም፤ የብዙዎች ስቃይ እና ለብቸኝነታቸው መንስኤ የሚሆንበት ሁኔታ ሰፊ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊት ናቸው፤ ናርሲስዝም ስያሜው ያገኘው እራሱን ከልክ በላይ የሚወድ ናርሲሰስ የሚባል ሰው የራሱን ምስል ለመሳም ሲሞክር በኩሬ ውስጥ ሰምቶ ህይወቱ ሊያልፍ በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡

በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከልክ በላይ እራስን የመውደድ የባህሪ እክል ካለ፣ በተወሰነ መጠን ቢሆንም ተፈጥሮ ለህመሙ እንደ መነሻ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላል ተብሏል፡፡

#የሚስተዋሉ ምልክቶች፤

• በፍጹም ለሌሎች ርህራሄ የለሽ መሆን
• በሌሎች ጉዳት ተጠያቂ መሆንን አለመፈለግ
• እሳቸውን ማዋደድ
• ከሌሎች በተለየ መልኩ እንክብካቤ ያስፈልገናል ብሎ ማሰብ
• ትችት የውስጥ ባዶነታቸውን ስለሚያሳያቸው ሊረበሹ እና ለበቀል ሊነሳሱ ይችላሉ
• ሰላለቸው ገነር ሁሌም ቢሆን ማውራትን ይወዳሉ
• ግሳፄን ወይም ትችትን አጥብቆ መፍራት
• አስታየቶችን እንደ ነቀፌታ እና ስድብ መቁጠር
• ስለ ግል ገጽታ አብዝቶ የመጨነቅ ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል ተብሏል፡፡

ባለሞያው እንደተናሩት በሁሉም ውስጥ በትንሹ ቢሆንም እራስን መውደድ ፣ እራስን ማድነቅ እና ስለ እራሰ በሌሎች ዘንድ መልካም ነገርን ማድመጥ ያስደስታል ብለዋል፡፡

ናርሲስትክ የሆኑ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግ እና የእቅዳቸውን ግብ ለማሳካት ሙሉ ትኩረተቸውን የሚሰጡ ሲሆን ብዙውን ጊዜም እቅዳቸውን ሲያሳኩ ይስተዋላሉ፡፡

• ናርሲሲስት የሆኑ ሰዎች በሰዎች ዘንድ ደግ ፣ ተጫዋች፣ አዛኝ እና ለሌሎች አሳቢ እንደሆኑ ተደርገው ሊታሰቡ ይችላሉ ፡፡
• ሃላፊነትን መውሰድ መቻል እና ጠንካራ የሆነ በራስ መተማመን ይታይባቸው
• አዘውትረው መዘነጥ ከቻሉ ደግሞ ውድ ቁሳቁሶችን መግዛትን ይመርጣሉ ተብሏል፡፡

#ህክምናው

ይህ አይነቱ ባህሪ ያላቸው ሰዎች ወደ ህክምና የማይመጡ ሲሆን፤ ለድብርት ለጭንቀት እና መሰል ተያያዥ ችግሮች የህክምና አገልግሎት ሲፈልጉ ህክምናን እንደሚያመሩ ተጠቁሟል፡፡ ህክምናው ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም ራስን ከልክ ባለፈ መልኩ የመውደድ ባህሪን በንግግር ህክምና ማከም እንደሚቻል ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

#ተግዳሮቶች

ይህ የባህሪ ችግር በትዳር አለም ውስጥ ከጥንዶቹ መካከል በአንደኛቸው ላይ የሚስተዋል ከሆነ ትዳሩ በፍቺ የሚጠናቀቅበት እድል መኖሩን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ እራሳቸውን ከልክ በላይ ስለሚያዋድዱ ብዙም ጓደኞችን ለማፍራት ይቸገራሉ፡፡

አፍቅሮተ እራስ ወይም ከፍተኛ የሆነ እራስ ወዳድነት ባህሪ ያለው የሥራ ባልደረባ እና አለቃ ካለ በሌሎች ላይ ስራ የመልቀቅ እድላቸው እንደዚሁ ይጨምራል ተብሏል፡፡

የናርሲስቲክ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ለእራሳቸው ባላቸው የተጋነነ በራስ መተማመን እና እራስ ወዳድነት ከሌሎች በተሸለ መልኩ አስፈላጊ እንደሆኑ እንዲሰማቸውም ይገደዳሉ፡፡፡

አስገራሚ ሊሆን ቢችልም ደካማ ጎናቸው ለራሳቸው ያላቸው ዝቅተኛ የሆነ በራስ መተማመን እና የበታችነት ስሜት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ታዲያ በዚህ ምክንያት ከሌሎች የሽንገላ አንደበትን፣ ውዳሴን እና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ እውቅና እንዲሁም ዝናን እንዲፈልጉ ይዳረጋሉ፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply