ኡበር በኬንያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሞተር ብስክሌቶችን ሊያሰማራ ነው

የከተማ ውስጥ የትራንስፖራት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው የኡበር ኩባንያ ኬንያ ውስጥ በሞተር ብስክሌት የማመላለሻ አገልግሎት ሊሰጥ ማሰቡ ተሰማ፡፡ ኡበር አገልግሎቱን ለመስጠት ያሰበው “ኦፒበስ” ተብሎ በሚታወቀው በስዊድናዊና ኬንያዊ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ድርጅት ጋር በመሻረክ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

3ሺ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሞተር ብስክሌቶችን እኤአ በ2020 ለማስገባት ማቀዱም የቪኦኤ ሪፖርተራችን ከናይሮቢ በላከው ዘገባ ተገልጿል፡፡ 

የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሞተር ብስክሌቶችን በኤሌክትሪክ ወደሚሰሩት የማዘዋወሩ ሂደት የአየር ብክለትን በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንሱ ይችላሉ ተብሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply