
ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የምፅዓትን ቀን ሽሽት ነው መባሉ ሐሰት መሆኑን የኛንጋቶም ወረዳ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። በደቡብ ኦሞ ዞን፣ የኛንጋቶም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ሎኪኛኒጋ ሙርሌ፣ ኡጋንዳውያኑ በወረዳቸው እንደሚገኙ አረጋግጠው፣ “አመጣጣቸው አካባቢውን ለማየትና የቤተክርስቲያን መልዕክት ለማድረስ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Source: Link to the Post